
የቢሮው አመሰራረት
መጀመሪያ በኢንቨስትመንት ኮሚሽን ስም በመቀጠል ደግሞ በንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ስር ተዋቅሮ የነበረው የኢንዱስትሪ ዘርፍ የመጨረሻ ግባቸው ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት የክልሉን ህዝቦች የልማቱ ተጠቃሚ በማድረግ የኑሮ ደረጃቸውን ማሻሻል ሆኖ እያለ በተለያየ ተቋም ስር በመደራጀታቸው አቅማቸው ከመበታተኑም በላይ በተግባርና ኃላፊነት መደራረብ ምክንያት ከአላስፈላጊ የጉልብትና ገንዘብ ብክነት በተጨማሪ አልፎ አልፎም ቢሆን በመገፋፋት ውጤታማ ስራ ሳይሰሩ ቆይተዋል፡፡ ስለሆነም ይህን ችግር በውል የተገነዘበው የአማራ ክልል ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 264/2011 አንቀጽ 10 እንደተደነገገው በንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ስር የነበረውን የኢንዱስትሪ ዘርፍና ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን በአንድ በማዋሃድ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮን አቋቁሟል፡፡
የተቋሙ ራዕይ
በ 2022 የክልሉ ኢኮኖሚ በኢንዱሰትሪ ላይ የተመሰረተ ሆኖ ማየት፡፡
የተቋሙን ተልዕኮ
የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋትና የዘርፉን ማነቆዎች በመለየት ለመፍትሄ የሚረዱ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎቸን በመቀመር ምቹ የሆነ የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት መሰረቱን በማስፋት የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ማሳደግ
የተቋሙን እሴቶች
ተጠያቂነት፥ተቋማዊ ኃላፊነት፥ የአገልግሎት ጥራት፥ግልፅና አሳታፊ፥ መልካም ስብዕና ያለው አመራር መፍጠር እና ሌሎችም ጥሩ ስብዕና ያለው ህብረተሰብ መፍጠር
አቶ እንድሪስ አብዱ
የአብክመ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ
መልዕክት
ክልላችን ሰፊ የሚታረስ መሬት÷አመቱን ሙሉ የሚፈሱ ወንዞች÷ገና ያልተነካ ሰፊ የመአድናት ክምችት÷ከፍተኛ የእንስሳት ሀብት÷ በዩኔስኮ የተመዘገቡትን ጨምሮ ለቱሪዝም መስህብነት የሚያገለግሉ ከፍተኛ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ቅርሶች ባለቤት እንዲሁም ሰራ ወዳድና ሰው አክባሪ ህዝብ ያለበት ክልል ነው።
የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮም ክልላችን ያለውን ሰፊ የሀብት መሰረቶች፣ በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ምቹ ሁኔታዎች በስፋት በማስተዋወቅና ጥቅም ላይ በማዋል ለዜጎች ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠር ፣የውጭ ምንዛሬ ግኝትን፤ የተኪ ምርት መጠንን እና የካፒታል ክምችትን በማሳደግ የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር ለማፋጠን አልሞ እየሰራ ያለ ተቋም ነው፡፡

አገልግሎቶች
የኢንቨስትመንት ፈቃድና ምዝገባ አገልግሎት
የኢንቨስትመንት መረጃ አገልግሎት
የኢንቨስትመንት ጥናትና ስርፀት
የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ድጋፍና ክትትል አገልግሎት
የኢንቨስትመንት ማበረታቻ መፍቀድ
ኢንቨስትመንት ማስተዋወቅና ማመቻቸት
የኢንቨስትመንት ዘርፎች
እንሰሳት ሀብት ልማት
ሰብል ልማት
አበባ፣አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ
ደን ልማት

ሆቴልና ቱሪዝም

ትምህርት

ጤና

የስፖርት ማዘውተሪያ

አይሲቲ
ማዕድንና ኢነርጂ ሀብት ልማት

ማዕድን ሀብት

ውሃና ኢነርጂ ሀብት
ኢንዱስትሪ ዘርፍ

በጨርቃ ጨርቅና ቆዳ ዘርፍ

በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብአት ዘርፍ

በእንጭትና ብረታ ብረት ዘርፍ

በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ
ኢንዱስትሪ ዞን

ደብረ ማርቆስ ኢንዱስትሪ ዞን

ደብረታቦር ኢንዱስትሪ ዞን
ዜናዎች
**************************************** ኢኢቢ: መጋቢት 30/2017 ዓ.ም (ባህር ዳር) በባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ከአሁን በፊት ገብተው ስራ ከጀመሩት...
Read More********************************** ኢኢቢ: መጋቢት 28/2017 ዓ.ም: ባህርዳር በመድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊና...
Read Moreየደሴ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ። ***************************************** ኢኢቢ፦ መጋቢት 28/2017ዓ.ም(ባህርዳር) በእለቱ አቶ...
Read More********************************************************** ኢኢቢ: የካቲት የካቲት 18/2017 ዓ.ም :ባህርዳር በደብረ ብርሃን ከተማ በ2 ቢሊየን 130 ሚሊየን ካፒታል...
Read More