- ይህ የኢንቨስትመንት ቀጠና በዋናነት የሚያጠቃልለው የምስ/ጎጃም ፣ምዕ/ጎጃምና ፣የአዊ ብሔረሰብ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ ወረዳዎችንና ከተሞችን ነው፡፡
- ይህ አካባቢ ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆን ከፍተኛ አድሮ በቂ ግብዓት በሌለበት አካባቢ ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ ማድረግ ባለሃብቶችን ለኪሳራ ሊዳርጋቸው ስለሚችል የአካባቢ ፀጋን መሰረት ያደረገ እና የመንግስትን የገንዘብ ብክነት በሚቀንስ መልኩ ቀጠናዊ የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጅን መከተል አስፈላጊ በመሆኑ ይህ የ10 ዓመት ኢንቨስትመንት ፍኖተ-ካርታ ተዘጋጅቷል፡፡
- በዚህ ፍኖተ-ካርታ መሰረት የክልሉ አካባቢዎች ያላቸውን ፀጋ መሰረት አድርገው በ6 ዋና ዋና የኢንቨስተመንት ቀጠናዎች ተከፍለዋል፡፡

- ቀጠናው ለአግሮፕሮሰሲን ማንፋክቸሪን ኢንዱስትሪዎች የሚሆን መሰረተ ልማት የተሟላለት ቡሬ የተቀናጀ የአግሮፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክን ማዕከል ያደረገ እና ሌሎች ሰባት መጋቢ የገጠር ሽግግር ማዕከላት በቻግኒ ፣በእንጅባራ፣ በዳንግላ፣ በመርሃዊ፣ በሞጣ፣በአማኑኤልና በፍ/ሰላም ያሉት ነው፡፡
- ስለሆነም የዚህ ቀጠና ቀዳሚ የኢንቨስትመንት ዘርፎች –
- የእንሰሳት ውጤቶችን (ስጋ፣ወተት፣ እንቁላል፣ማር፣የቆዳ ውጤቶች መፈብረክ)
- ምግብ ማቀነባበር (የምግብ ዘይት፣ስታች ፣ግሉኮስ ፣ፓስታ፣ ማካሮኒ፣ ብስኩት፣አልሚ ምግቦች…ወዘተ ማቀነባበር)
- የደን ውጤቶችን መፈብረክ (ኤምዲአፍ/አችዲኤፍ፣ ችፑድ፣ ኮምፖርሳቶ፣ ወረቀት…ወዘተ) ናቸው፡
