የአባይ ሸለቆ ኢንዱስትሪ ልማት ቀጠና ይህ የኢንዱስትሪ ልማት የአባይ ሸለቆንና የገባሮቹን (የጀማ፣በሸሎ፣… ወዘተ) አካባቢዎች ያካትታል፡፡ ቀጠናው በዋናነት አባይ ሸለቆ እና ከላይ የተጠቀሱ ወንዞችን የሚያዋስኑ የሰ/ሸዋ ፣ደ/ወሎ፣ደ/ጎንደር፣ምስ/ጎጃም እና ሰ/ወሎ ከፊል አካባቢዎችን የካትታል ይህ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የማዕድን ክምችት ማለትም ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ እንደ ሲሊካ ሳንድ፣ላይምስቶን፣ግራናት፣ጅፕሰም፣ኳርትዝ፣ ዕምነበረድ…ወዘተ በአለም ገበያ ተፈላጊ የሆኑ እንደ ኦፓል፣አምበርና… የመሳሰሉ የከበሩ ማዕድናት እና የኮንስትራክሽን ግብዓት የሚሆኑ ማዕድናት በስፋት የሚገኝበት አካባቢ ነው ስለሆነም የአባይ ሸለቆ ኢንዱስትሪ ልማት ቀጠና የቅድሚያ-ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘርፎች የማዕድን ፍለጋና የማዕድን ምርቶችን የሚያቀነባብሩ የማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፎች ናቸው፡፡ ሲሚንቶ፣መስታወት፣ብርጭቆ፣ጠርሙስ፣ጅፕሰም፣ሴራሚክ፣እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ግብዓት እና ከበሩ ማዕድናትን የሚያስጌጡ ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉበት የሚፈለግ ቀጠና ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ