**********************************
በመድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ዩሐንስ አማረ እንደገለፁት በየደረጃው የሚገኙ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የሚያጋጥሟቸውን ማነቆዎች በመፍታት የፕሮጀክቶችን የማምረት አቅም ማሳደግ እንዲሁም አዳዲስና የተሻለ የስራ ልምድና የፋይናንስ አቅም ያላቸውን ባለሃብቶች መሳብ መቻል የመድረኩ ዋና አላማ ነው ብለዋል።
በመሆኑም እንደ ክልል በዘርፉ የሚስተዋሉ የአሰራር ማነቆዎችን በመፍታት በአንድ ማዕከል የተደራጀ የኢንቨስትመንት አገልግሎት መስጠት በመጀመራችን በክልሉ ባለፉት ወራቶች ከ1 ሺ 500 በላይ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል።
ያለ ኢንቨስትመንት ዘላቂ ልማት ማረጋገጥ አይይቻልም ያሉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አወቀ አስፈሬ የስራ እድል ለመፍጠርና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ የግሉን ዘርፍ መደገፍ ያስፈልጋል።
በመሆኑም በዘርፉ በግል፣ በመንግስትና በባለ ድርሻ አካላት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለይተን በመፍታትና በዞናችን ያለውን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጭ በመጠቀም እንዲሁም የዞናችን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በማጠናከር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።
የዞኑ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምርያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ያብስራ እሸቴ የዞኑ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የሚገኝበት አሁናዊ ሁኔታና አጠቃላይ በዘርፉ የሚስተዋሉ ማነቆዎችና ምቹ ሁኔታዎችን አስመልክተው የመወያያ ፁሁፍ አቅርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል።
በመድረኩ በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ ባለሃብቶች፣ ኢንተርፕራይዞች፣ ሃብት መፍጠር የቻሉ ሞዴል አርሶ አደሮች የህብረት ስራ አመራሮችና ሌሎች አጋር አካላት ተሳትፈዋል።