የኢንቨስትመንት ፈቃድ ምትክ፣ ለውጥ፣ ዝውውርና ማስተላለፍ
ለምትክ ኢንቨስትመንቱ ፈቃዱ ለሁሉም የኢንቨስትመንት ቅርጾች
- የማመልከቻ ደብዳቤ
- የኢንቨስትመንት ፈቃዱ የጠፋ ከሆነ ስለ መጥፋቱ ከፖሊስ ማስረጃ
- የኢንቨስትመንት ፈቃዱ የተቀደደ ወይም የተበላሸ ከሆነ የተበላሸውን ወይም የተቀደደውን የኢንቨ/ፈቃድ ማቅረብ /ፈቃዱም የተሰረዘ መሆን የለበትም/
- የታደሰ የኢን/ፈቃድ ወይም ማምረት/አገልግሎት መስጠት ከጀመረ የንግድ ስራ ፈቃድ
- የባለሃብቱ መተወቂያ
- የአገልግሎት ክፍያ 100 ብር
- የማመልከቻ ቅጹን የሞላው በወኪል ከሆነ የውክልና ስልጣን ማረጋገጫ ሰነድ ፎቶ ኮፒ
ለለውጥ ኢንቨስትመንቱ ፈቃዱ ለሁሉም የኢንቨስትመንት ቅርጾች
- የማመልከቻ ደብዳቤ
- የንግድ ስራ ፈቃድ ያለወጣ መሆን አለበት
- የታደስ የኢንቨ/ፈቃድ /ፈቃዱም የተሰረዘ መሆን የለበትም/
- የኢንቨስትመንት ፈቃዱ የካፒታል ለውጥ ከሆነ የካፒታል ለውጥ ማስረጃ
- የኢንቨስትመንት ፈቃዱ የአድራሻ /ቦታ/ ለውጥ ከሆነ ከመጣበት ቦታ በድጋፍ ደብዳቤ ሙሉ ፋይሉ
- የኢንቨስትመንት ፈቃዱ የዘርፍ ለውጥ ከዋናው ሳይወጣ ከሆነ በነባሩ ፕሮጀክቱ በማበረታቻ የተቀበለውን ወደ መመለስ ወይም ወደ አዲሱ የቀየረበትን ማስረጃ
- የኢንቨስትመንት ፈቃዱ የስም ለውጥ ከሆነ ህጋዊ ማስረጃ
- የባለሃብቱ መተወቂያ
- የአገልግሎት ክፍያ 100 ብር
- የማመልከቻ ቅጹን የሞላው በወኪል ከሆነ የውክልና ስልጣን ማረጋገጫ ሰነድ ፎቶ ኮፒ