
- Phone no -0583208350
- E-mail address - amharaindustryandinvestment@gmail.com
- Telegram- link
የቢሮው ኃላፊ መልዕክት
ክልላችን ሰፊ የሚታረስ መሬት÷አመቱን ሙሉ የሚፈሱ ወንዞች÷ገና ያልተነካ ሰፊ የመአድናት ክምችት÷ከፍተኛ የእንስሳት ሀብት÷ በዩኔስኮ የተመዘገቡትን ጨምሮ ለቱሪዝም መስህብነት የሚያገለግሉ ከፍተኛ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ቅርሶች ባለቤት እንዲሁም ሰራ ወዳድና ሰው አክባሪ ህዝብ ያለበት ክልል ነው።
የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮም ክልላችን ያለውን ሰፊ የሀብት መሰረቶች፣ በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ምቹ ሁኔታዎች በስፋት በማስተዋወቅና ጥቅም ላይ በማዋል ለዜጎች ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠር ፣የውጭ ምንዛሬ ግኝትን፤ የተኪ ምርት መጠንን እና የካፒታል ክምችትን በማሳደግ የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር ለማፋጠን አልሞ እየሰራ ያለ ተቋም ነው፡፡ በመሆኑም በክልላችን በጨርቃ ጨርቅና ቆዳ፣ በእንጨትና ብረታብረት፣ በኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓት፣ በአግሮፕሮሰሲንግ፣ በግብርና ልማት፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ በማዕድንና ኢነርጂ፣ በቴክኖሎጂ ልማት÷ በእንሰሳት፤ አበባና ፍራፍሬ /ሆልቲካልቸር/ ልማት መሰማራት ለምትፈልጉ አልሚዎች ክልላችን እጅግ ብዙ እምቅ ሀብቶች ያሉት በመሆኑ ወደ ክልላችን መጥታችሁ ኢንቨስት እንድታደርጉ እያልኩ ክልላችን የባለሀብቶችን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ መሰረተ ልማትና የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተሟላላቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በባህር ዳር፣ በኮምቦልቻ፣ በደብረብርሃንና በቡሬ ከተሞች ገንብቶ ለባለሃብቶች በማስተላለፍና ባለሀብቶችን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በተለይ በአግሮ ፕሮሰሲንግ ማለትም በስታርች፣ በግሎኮስ፣በስጋ፣በወተት፣በማር፣በፍራፍሬ እና በሌሎች የግብርና ምርቶች ማቀነባበር ዘርፍ መሰማራት የምትፈልጉ ባለሃብቶች፤ እንዲሁም በጨርቃ ጨርቅ ቆዳና አልባሳት መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች፤ በአጠቃላይ በአምራች ኢንዱስትሪውና በሌሎች ኢንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራት የምትፈልጉ ባለሀብቶች በክልላችን መሰረተ ልማት በተሟላላቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥም ሆነ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ውጭ በከተሞች እና በከተሞች ዙሪያ ባሉ ለኢንቨስትመንት ተለይተው በተከለሉ ቦታዎች ገብታችሁ ኢንቨስት እንድታደርጉ ስጋብዛችሁ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል፡፡
ክልላችን ለባለሃቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ፈጣን ፣ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ ከዚህ በፊት በዞኖችና በተወሰኑ ከተሞች ብቻ ተወስኖ የነበረውን አደረጃጀት እስከ ወረዳና ከተሞች ከመዘርጋቱ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑና የባለሀብቱን እንግልትና ውጣ ወረድ የበለጠ ለመቀነስ ሲባል አገልግሎቱን ቀልጣፋ÷ግልጽና ፍትሀዊ ሊያደርጉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን አስለምቶ ወደ ስራ እየገባ ያለ መሆኑን ሳሳውቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው ፡፡ አማራ ክልል ሰርተው የሚኮሩበት ፣ነግደው የሚያተርፉበትና በሠላም የሚኖሩበት ክልል ስለሆነ ወደ ክልላችን መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል፡፡