“ሰላምን በማረጋገጥ ኢንዱስትሪዎች 24 ሰአት መስራት እንዲችሉ ማድረግ ይገባል”

**********************************************************

ኢኢቢ: የካቲት የካቲት 18/2017 ዓ.ም :ባህርዳር

በደብረ ብርሃን ከተማ በ2 ቢሊየን 130 ሚሊየን ካፒታል የተገነቡ 5 ፋብሪካዎች ተመረቁ

አዲስ ወደ ስራ የገቡት ፋብሪካዎች ለ2ሺህ ስራ ፈላጊ ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ ያደርጋሉ ሲሉ የደብረ ብርሃን ከተማ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ አቶ ብርሃን ገብረሂዎት ገልጸዋል ።

አብዛኞቹ ፋብሪካዎች የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሬን የሚያስቀሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በዚህ በጀት አመት 17 ኢንዱስትሪዎች እንደሚመረቁም አመላክተዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል እንዳነሡትም በሶስት አመት ውስጥ 48 ፋብሪካዎች ወደ ስራ ገብተዋል ብለዋል።

ለ8 ሺህ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር መቻላቸውን ጠቅሰዋል።

120 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ፋብሪዎች በከተማው እንደሚገኙ ጠቁመው

ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ሲገቡ ለ1 መቶ 12 ሺህ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ይችላሉ ብለዋል።

11 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡ 17 ኢንዱስትሪዎች በዚህ በጀት አመት እንደሚመረቁ ጠቅሰዋል።

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ እንዳነሡት ክልላችን ሰፊ የሚለማ መሬትን ጨምሮ በርካታ የተፈጥሮ ሀብት ያሉት መሆኑን ጠቅሰው እነዚህ ለኢንቨስትመንት ምቹ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ታምርት እሳቤ በዚህ በጀት አመት ከፍተኛ መነቃቃትን ፈጥሯል በ7 ወር 1መቶ 11 በአዲስ ወደ ምርት አስገብተናል ብለዋል።

የኢንቨስትመንት ተቋማት በየደረጃው እንዲናበቡ ተደርጓል ውስብስብ የአገልግሎት አሰጣጥን በዚህ 7 አመት አሻሽለናል ሲሉ ጠቅሰው በዚህ በጀት አመት ከ9 መቶ በላይ የኢንቨስትመንት ጥያቄ መልሰናል ሲሉ ጠቅሰዋል።

በ6 ወራት ዘርፉ ከ91 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን ተናግረዋል።

የኢፌደሪ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እንዳሉት ዛሬ የተመረቁት ፋብሪካዎች የሀገር ኤስፖርት በማሳደግ የሀገር ፣ የከተማውን፣ የአካባቢውን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል።

ከ2010 በጀት አመት በፊት የሰሜን ሸዋ ዞንን ጨምሮ በደብረ ብርሃን ከተማ 18 ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ጠቅሰው

በሶስት አመት ውስጥ 48 ኢንዱስትሪዎች በደብረ ብርሃን ቀጣና ተመርቀው ስራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ታምርት አማራ ክልል የተሻለ መሆኑን አንስተው በኢንቨስትመንት ምሳሌ የሆነችው ደብረ ብርሃን ከተማ መሆኗን ገልጸዋል።

ሰላምን በማረጋገጥ ኢንዱስትሪዎች 24 ሰአት መስራት እንዲችሉ ማድረግ እንደሚገባ አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ፕሮግራም ለኢንቨስትመንቱ እድገት መሠረት መሆኑን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL

Website- http://www.investinamhara.gov.et/

YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg

WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo

Twitter- https://x.com/amhara_and77292

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top