የተቋሙ ስልጣን፤ተግባርና ኃላፊነት

የአማራ ክልል ምክር ቤት በተሻሻለው የብሔራዊ ክልሉ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 49 ንዑስ
አንቀጽ 3 (1)ድንጋጌ ስር በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሻሻለው የአስፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያና ሥልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ አንቀጽ 10 መሰረት ከተቋቋመ በኋላ በአዋጅ ቁጥር 280/2014 አንቀጽ 15 መሰረት ተቋሙ የሚከተሉት ስልጣን፤ ተግባርና ኃላፊነት አለው

  1. በክልሉውስጥየኢንዱስትሪተቋማትእንዲያብቡናእንዲስፋፉያበረታታል፣ይደግፋል፣
    የጥናት፣ የስልጠና፣ የቴክኒክና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል፤
  2. የማኑፋክቸሪንግዘርፉንበመደገፍረገድቁልፍሚናካላቸውየክልሉናየፌደራሉአስፈፃሚአካላትምሆነየከፍተኛትምህርትናምርምርተቋማትጋርየጋራዕቅዶችንአውጥቶይሰራል፤
  3. አግባብካላቸውየመንግሥትአካላትጋርበመተባበርበክልሉውስጥበማኑፋክቸሪንግ
    ዘርፉ ለሚሰማሩ አነስተኛ፣መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት ሊውሉ
    የሚችሉ የኢንዱስትሪ መንደሮችን፣የክላስተር ማእከላትንና የኢንዱስትሪ ልማት ፓርኮችን ያደራጃል፣ለነዚሁ የሚያስፈልገው መሬት ከሶስተኛ ወገኖች ይዞታ ነጻ እንዲሆን ከሚመለከተው አካል ጋር ይሰራል፣የቦታ ካርታና ፕላን በማሰራትም ሆነ እስከየ መዳረሻቸው የሚዘልቅ መሠረተ-ልማት እንዲሟላላቸው በማድረግ ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያስተላልፋል፤
  4. በክልሉውስጥየአምራችኢንዱስትሪዎችንሁለንተናዊአቅምለማሳደግየኢንዱስትሪ
    ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ ይሰጣል፣ የድጋፍ ማእቀፎችን ያዘጋጃል፤
  5. የአምራችኢንዱስትሪያሊስቶችአቅምየሚገነባባቸውንተቋማትያደራጃል፣ይደግፋል፣
    የእዉቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማእከላት ሆነው እንዲያገለግሉ ያደርጋል፤
  6. ኢንዱስትሪያሊስቶችንለመፍጠርወይምበስራላይየሚገኙትንለማጠናከርየሚረዳ
    ክልል አቀፍ የኢንተርፕሬነርሽፕ ፕሮግራም ቀርጾ በስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
    ስልጠናዎችን ይሰጣል፤
  7. ለአምራችኢንዱስትሪዎችመስፋፋትዘላቂፋይዳያለውየአዋጭነትጥናትናየፕሮጀክትትግበራ፣ክትትልናድጋፍሥርዐትቀርፆገቢራዊያደርጋል፤
  8. ከአምራችኢንዱስትሪውዘርፍበኩልየሚቀርቡለትንፕሮጀክቶችይቀበላል፣ወደየ
    ክላስተር ማእከላት፣የኢንዱስትሪ መንደሮች ወይም ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ሊገቡ
    የሚችሉትን በአይነት ይለያል፣ የየፕሮጀክቶቹን ፕላንት ሌይአውት ይገመግማል፣
    የሚያስፈልጋቸውን የመሬት መጠን ይወስናል፤
  9. የአነስተኛናየመካከለኛአምራችኢንዱስትሪዎችየዘርፍማሕበራትእንዲደራጁ
    አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፤
  10. የኢንዱስትሪፕሮጀክትሀሣቦችንበየጊዜውእያመነጨበሚገባተጠንተውበሥራላይ
    ሊውሉ የሚገባቸውን በመለየት አግባብ ላለው የፌደራል መንግሥት አካል ያስተላልፋል፣ በክልሉ አቅም ሊፈፀሙ የሚችሉት ደግሞ በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤
  11. በማኑፋክቸሪንግኢንዱስትሪውዘርፍከአነስተኛወደመካከለኛ፣ከመካከለኛወደከፍተኛ
    ደረጃ የሚሸጋገሩ ባለሃብቶች በተሸጋገሩበት ዘርፍ እድገታቸው እንዲፋጠን ለማድረግ
    የማምረቻ ቦታና የመሠረተ-ልማት አገልግሎት እንዲሟላላቸው ይሠራል፣በፕሮጀክት
    ዝግጅትም ሆነ በአዋጭነት ጥናት ረገድ ይደግፋል፤
  12. በክልሉውስጥቀላል፣መካከለኛናከፍተኛኢንዱስትሪዎችእንዲስፋፉተስማሚ
    ቴክኖሎጅዎችና አዳዲስ የአሠራር ዘዴዎችን በመቀየስ የዘርፉ የመወዳደር አቅም
    እንዲጎለብት ይሠራል፤
  13. በክልሉውስጥየገጠርኢንዱስትሪያላይዜሽንንለማስፋፋትበያካባቢውያለውን
    የመልማት አቅም መሠረት ያደረጉ የኢንዱስትሪ ዓይነቶችን ይለያል፣ የኢንዱስትሪ
    መንደሮችን ያደራጃል፣ ተፈላጊው መሠረተ-ልማት እንዲሟላላቸው ያደርጋል፤
  14. የአነስተኛናየመካከለኛማኑፋክቸሪንግኢንዱስትሪዎችንለማስፋፋትየሚረዱምርጥ
    ተሞክሮዎችን ያሰባስባል፣ ይቀምራል፣ ለተጠቃሚዎች ያሰራጫል፤
  15. በክልሉውስጥምቹናተወዳዳሪየኢንቨስትመንትከባቢእንዲፈጠርየሚያበረታቱ
    የፖሊሲ ሀሣቦችን ያመነጫል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፤
  16. በክልሉውስጥየሚገኘውንየሀብትክምችትናየኢንቨስትመንትእድልመረጃዎች
    ያሠባስባል፣ ያጠናቅራል፣ በመረጃው መሠረት ክልላዊ የኢንቨስትመንት መሪ እቅድ እና
    ተያያዥ እቅዶችን ያዘጋጃል፣ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ይወስናል፣ መረጃዎችን
    ለባለሀብቶች ያሠራጫል፣ ተጨባጭ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ለነዚሁ ወገኖች
    ያስተዋውቃል፤
  17. በሚለከተውአካልተለይቶበተዘጋጀውየኢንዱስተሪቀጠናአምራችኢንዱስትሪዎች
    እዲስፋፉ ይሰራል፣የቀጠናወቹ ወሰንና ያጠቃቀም ለውጥ በመሬት አስተዳደር መስሪያ ቤቱ እዲመዘገብ ያደርጋል፣
  18. ከዚህበላይበንኡስአንቀጽ17 በተደነገገውመሰረትየመሬትአጠቃቀምእቅድያዘጋጃል፣
    ወደ ቀጠናው እንዲገቡ ለተመረጡ አልሚዎች ውል ይዞ መሬት ያስተላልፋል፣
    እንዳስፈላጊነቱ የመሠረተ-ልማት ማሟላት ተግባራትን ያከናውናል፣ በመሬት አጠቃቀም
    እቅዱ መሠረት በማያለሙት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል፣መሬቱን ተመላሽ በማድረግ
    ለሌላ አልሚ ያስተላልፋል።
  19. የተሻለየኢንቨስትመንትፍሰትባለባቸውእናበሌሎችበጥናትበሚለዩየክልሉ
    አካባቢዎች እንዲሁም በልዩ የኢኮኖሚ ቀጠናዎች ለግል ባለሀብቱ የተከለለ አገልግሎት
    የሚሰጡ የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫዎችን ያቋቁማል፤
  20. ኢንቨስትመንትንከማስፋፋትናከማበረታታትጎንለጎንየክልሉንመልካምገጽታ
    ለመገንባት የሚረዱ ጽሑፎችንና ፊልሞችን ያዘጋጃል፣ ያሠራጫል፣ አውደ-ርዕዮችን፣
    ዐውደ-ጥናቶችንና ሴሚናሮችን እንዳስፈላጊነቱ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር
    ያካሂዳል፣ በተዘጋጁ ተመሳሳይ ፕሮግራሞች ላይ ይሳተፋል፣ ሥልጠናዎችን ይሰጣል፤
  21. ስለኢንቨስትመንትየወጡሀገርአቀፍፖሊሲዎችናሕጎችበክልሉውስጥበትክክል
    ሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፤
  22. በባለሀብቶችየሚቀርቡለትንየኢንቨስትመንትጥያቄዎችመርምሮአግባብባላቸው
    የኢንቨስትመንት አዋጆችና ደንቦች ላይ የተደነገጉትን ተፈላጊ ሁኔታዎች አሟልተው
    ሲገኙ በተሰጠው የሥልጣን ክልል መሠረት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ይሰርዛል፣ ከነዚሁ ግልጋሎቶች የሚመነጨውን የአገልግሎት ክፍያ ይሠበስባል፤
  23. በክልሉውስጥበኢንቨስትመንትሥራየተሰማሩባለሀብቶችንያበረታታል፣ይደግፋል፣
    ፈጥነው ወደ አፈፃፀም በማይገቡ ፕሮጀክቶች ላይ ደግሞ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት
    ጋር በመተባበር ፈቃድ የመሠረዝና መሬት የማስመለስ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳል፣እንዲወሰዱ ያደርጋል፤
  24. የኢንቨስትመንትፈቃድየተሠጣቸውባለሀብቶችየሚያቀርቧቸውየማበረታቻጥያቄዎች
    ሕጉ ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች አሟልተው የቀረቡ መሆናቸውን እያረጋገጠ ተገቢውን ውሣኔ ይሠጣል፤
  25. በባለሀብቶችናጉዳዩበሚመለከታቸውየክልልመስተዳድሩአካላትመካከል
    የኢንቬስትመንት ተግባራትን ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፤
  26. በክልሉውስጥየሚካሄደውንየኢንቨስትመንትእንቅስቃሴአስመልክቶለባለሀብቶች
    ተገቢውን የምክርና የመረጃ አገልግሎት ይሰጣል፤
  27. ጉዳዩከሚመለከታቸውአካላትጋርበመተባበርበፌደራሉመንግሥትየኢንቨስትመንት
    ኮሚሽን በኩል ፈቃድ አግኝተው በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን የሃገር ውስጥም ሆነ
    የውጭ ባለሃብቶች ተግባራት በቅርብ ይከታተላል፣የባለሃብቶች ፎረም እንዲቋቋም
    ይረዳል፣ ድጋፍ ይሰጣል፣ትክክለኛ የሥራ እንቅስቃሴ ላይ የማይገኙትን መሬቱን ነጥቆ
    ውሳኔውን ለክልሉ መሬት ቢሮ እና ለፌደራል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያሳውቃል፤
  28. የኢንቨስትመንትፈቃድየተሰጣቸውንፕሮጀክቶችአፈፃፀምበቅርብይከታተላል፣
    የኢንቨስትመንት ፈቃዱ የያዛቸው ሁኔታዎች መከበራቸውንና የተሰጡ ማበረታቻዎችም
    ለታለሙላቸው ዓላማዎች መዋላቸውን ያረጋግጣል፣ በፕሮጀክት ሀሳባቸው ቃል የገቡትንየቴክኖሌጅ ሽግግር ፣ካፒታል እና የሥራ እድል ተግባራዊ እንዲያደርጉ ይከታተላል፣ተግባራዊ የማያደርጉትን እርምጃ ይወስዳል፤
  29. ለኢንቨስትመንትመስፋፋትየሚረዱልዩልዩማትጊያዎችንበማጥናትለክልሉ
    መስተዳድር ምክር ቤት ያቀርባል፣ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን
    ይከታተላል፤
  30. ባለሀብቶችበዚህአዋጅናአዋጁንለማስፈጸምበሚወጡደንቦችናመመሪያዎችይዘት
    ላይ የሚኖራቸው ግንዛቤ ከጊዜ ወደጊዜ እንዲዳብር ያደርጋል፤
  31. አግባብነትካላቸውየክልሉናየፌደራሉመንግሥትአካላትጋርበመተባበርለአምራች
    ኢንዱስትሪዎችና ለኢንቨስትመንት መስፋፋት እንቅፋት የሚሆኑ ማነቆዎች ተለይተው
    እንዲፈቱ ያደርጋል፤
  32. ጉዳዩከሚመለከታቸውአካላትጋርበመቀናጀትየድህረ-ኢንቨስትመንትድጋፍናክትትልሥራዎችንያከናውናል፤
  33. በክልሉውስጥበአምራችኢንዱስትሪዘርፍየመልማትእድልያላቸውንአካባቢዎች
    ይለያል፣ አካባቢዎቹ የሚለሙበትን ስልት ይቀይሳል፤
  34. የኢንቨስትመንትፕሮጀክቶችወደሥራእንዲገቡከፋይናንስተቋማትጋርበመተባበር
    የብድር አገልግሎት እንዲመቻችላቸው ያደርጋል፡፡
Scroll to Top