ሰሜን ምዕራብ አማራ ኢንዱስትሪ ልማት ቀጠና

  • ይህ የኢንዱስትሪ ልማት ቀጠና የሰ/ጎንደር፣የምዕ/ጎንደር፣ጎንደር ከተማ እና ከፊል የማዕከላዊ ጎንደር ዞኖችን የሚያካልል ነው፡፡
  • አካባቢው በተለይ በምዕ/ጎንደርና ከፊል ሰሜን ጎንድር ከፍተኛ የሆነ የቅባትና የጭረት ምርቶች (ሰሊጥ፣ሱፍ፣በሎቄ፣ጥጥ፣…ወዘተ) እና ሰፊ የእንሰሳት ሀብት ያለው፣ በጎንደር ከተማና ሰ/ጎንደር ደግሞ በዩኔስኮ የተመዘገቡ ሰፊ የቱሪስት መስህብ ሀብቶች ያሉበት ቀጠና ነው፤
  • ለአብነት ሰሜን ብሔራዊ ፓርክ፣የአፄ ፋሲለደስ ቤተ-መንግስት ፣አላጥሽ ብሔራዊ ፓርክ እና ፣እንደ ዋሊያ አይቤክስና ጭላዳ ባቡን ያሉ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ብርቅ  እንሰሳት…የሚገኙበት ነው፡፡
  • ስለሆነም ፡-
  • ዘመናዊ የቅባት እህሎችና ጥጥ  ማምረት
  • የሆቴልና ቱሪዝም ስራዎች
  • እንሰሳት እርባታና ማድለብ
  • አግሮፕሮሰሲንግና ቴክስታይል በቀጠናው ቅድሚያ የሚሰጣቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎች ናቸው፡፡

ሰሜን ምዕራብ አማራ ኢንዱስትሪ ልማት ቀጠና

 ዘመናዊ የቅባት እህሎችና ጥጥ ማምረት  የሆቴልና ቱሪዝም ስራዎች  እንሰሳት እርባታና ማድለብ  አግሮፕሮሰሲንግና ቴክስታይል  በቀጠናው ቅድሚያ የሚሰጣቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎች ናቸው፡፡

Scroll to Top