“ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” በሚል መሪ ቃል

የደሴ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።

*****************************************

ኢኢቢ፦ መጋቢት 28/2017ዓ.ም(ባህርዳር)

በእለቱ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የምክር ቤት አባልና የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ፣ አቶ ተፈሪ ታረቀኝ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ አሸናፊ አለማየሁ የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የከተማ አመራሮችና የከተማዋ ነጋዴ ባለኃብት በተገኙበት ውይይቱ ተካሂዷል።

አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በመክፈቻ ንግግራቸው የንቅናቄ መድረክ ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር በኢንዱስትሪ ከተሰማሩ የከተማችን ባለሃብቶች ጋር ስራውን በመገምገምና በመወያየት ከፍ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለሃብቱ ወደ አምራች ኢንዱስትሪው በስፋት እንዲቀላቀሉ በማድረግ ለከተማችንም ህብረተሰብ የስራ ዕድል በመፍጠር በጋራ ከተማችንን ለማሳደግ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል።

ለስራው አስቸጋሪ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ሚፈታበትን መንገድ በጋራ በመፍጠር የተሻለ ኢኮኖሚ እንዲኖር መስራት ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል።

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ ታረቀኝ በዕለቱ ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት የሚለው የንቅናቄ መድረክ አምራች ኢንዱስትሪውን ለማበረታትና ለማሳደግ የታሰበ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደክልላችን በጸጥታው ችግር የወደሙና የተዘጉ ድርጅቶች ችግራቸውን በቅንጅት በመፍታት ወደ ስራ እንዲገቡና የተሻለ እንቅስቃሴ እንዲኖር ተደርጓል። ለበርካታ ዜጎችም ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል።

ደሴ ከተማ በርካታ መሰረተ ልማት እየተሟላላት በመሆኑዋ ይህም ጠንካራ አመራርና ልማት ወዳድ ህዝብ በመቀናጀቱ በመሆኑ በቀጣይም በከተማዋ ላይ ኢንቨስት በማድረግ በኢንዱስትሪው ያደገች ከተማ መፍጠር ይጠበቃል ሲሉ አቶ ተፈሪ ታረቀኝ ገልፀዋል።

አቶ አለባቸው ሰይድ በደሴ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ በከተማችን በርካታ አምራች ኢንቨስተመንት እየተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

በዕለቱ ፕሮግራም ባለሃብቱ እያጋጠመው ያለውን ችግር በመወያየት ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ለመፍታት እና የከተማዋን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ምርቶችን ከማስመጣት በደሴ ከተማ ላይ ማምረት ለማስቻል መሆኑን ተናግረዋል።

ከተማዋ ሰላም መሆንዋ፣ ለልማትም ምቹ ከተማ እና እያደገች ያለች ከተማ በመሆኗ በርካታ ባለሃብቶችን ወደ ስራው ለማስገባት እየተመቻቸ በመሆኑ ወደ አምራች ኢንዱስትሪ በመቀላቀል ህብረተሰቡ፣ ከተማዋና ባለሃብቱ በጋራ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ መፍጠር ይጠበቃል ሲሉ አብራርተዋል።

ተሳታፊ ባለሃብቶች በበኩላቸው ደሴ ከተማ እየተሰራ ያለው ልማትና ቅንጅታዊ ስራ የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪ ለመቀላቀል በጋራ ተደራጅተን እየሰራን ነው የበለጠ ወደ ተሻለ የኢኮኖሚ ደረጃ ለመሻገርና በስፋት የስራ ዕድል ለመፍጠር ከመንግስት አካል ጋር ተቀናጅተን ለመስራት ዝግጁ ነን ሲሉ ገልጸዋል።

በመጨረሻም የተሻለ የምርት እንቅስቃሴ ላይ ያሉ ባለሃብቶችና ድርጅቶች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል። ዘገባው የደሴ ከተማ ኮሚኒኬሽን ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top