በጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራው አንበሳ ኢሊት ታክቲካል ቴክስታየል ምርት ማምረት ጀመረ!

****************************************

ኢኢቢ: መጋቢት 30/2017 ዓ.ም (ባህር ዳር)

በባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ከአሁን በፊት ገብተው ስራ ከጀመሩት አራቱ ኢንዱስትሪዎች በተጨማሪ የክልሉ መንግስት ብሎም የባህርዳር ከተማ አስተዳድር ከእስራኤል ሀገር ባለሀብቶች ጋር አብሮ ለመስራትና በክልላችን እስራኤላዊያን መጥተው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በተደጋጋሚ ጊዜ በተደረጉ ይፋዊ የስራ ጉብኝቶች እና የባለሀብት ውይይቶች ውጤት የሆነው፤ ለፓርኩ አምስተኛው ኢንዱስትሪና በእስራኤል ባለሀብቶች ከ 3 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት “አንበሳ ኢሊት ታክቲካል ቴክስታየል ኀ.የተወሰነ ማህበር” ምርት መጀመሩን አስመልክቶ ይፋዊ የስራ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በዛሬው እለት ተከናወነ፡፡

በይፋዊ የስራ ማስጀመሪያ መርሀ ግበሩ የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱን ጨምሮ የባህርዳር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው፤ የባህርዳር ምክትል ከንቲባ አቶ አስሜ ብርሌ፤ የከተማው ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መመሪያ ሃላፊ ወ/ሮ ብርሀን ንጉሴ፤ በዘርፉ ኢንቨስት ያደረጉት የእስራኤል ባለሀብቶችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

አንበሳ ኢሊት ታክቲካል ቴክስታየል ኢንዱስትሪ ደረጃቸውን የጠበቁ የአሜሪካና እስራኤል ስታንዳርድን የጠበቁ አልባሳትን የሚያመርት ድርጅት ሲሆን በአጭር ጊዜ በባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ሸድ ተረክቦ ወደ ምርት በመግባት በአሁኑ ሰአት አርባ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ ለወጣቶች ተገቢውን ስልጠና በመስጠት አስከ አምስት መቶ ለሚጠጉ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በስራ ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ተገኝተው ሀሳብ የሰጡት የቢሮው ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱና የከተማወ ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው በንግግራቸው በተመሳሳይ ኢንዱስትሪው ስራ እድል ከሚፈጥሩ ዘርፎች አንዱ እንደመሆኑ፤ አዳዲስ ቴክኖሎጂ በማስገባት ለሀገራችን የሚያስተዋውቅ እንደመሆኑ፤ የመንግስት ስትራቴጂን በማስፈጻም በኩል ተኪ ምርትን በማምረት የማይተካ ሚና ያለው ኢንዱስትሪ በመሆኑ በቅርበት ድጋፍን ክትትል እንደሚደረግላቸውና ባለሀብቶቹም ይህን ድጋፍ ተጠቅመው ከዚህ የተሸለ ስራቸውን በማስፋትና አቅም ፈጥረው ውጤታማ እንደሚሆኑና በክልላችን ብሎም በሀገራችን ኢኮኖሚያዊ እድገት ሚናቸውን እንደሚወጡ በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

የአንበሳ ኢሊት ታክቲካል ቴክስታየል ኢንዱስትሪ በበኩሉ የተሰጡ አስተያየቶችን ወስዶ በየደረጃውና በየዘርፉ የሚገኘው አማራር ድጋፍና ክትትል የሚያደርጋለቸው ከሆነ በአጭር ጊዜ ስራውን በማስፋት፤ የኢንዱስትሪውን የማምረት አቅም በማሳደግ ምረቱን ከሀገር ውስጥ ገቢያ አልፎ በምስራቅ አፍሪካ ለሚገኙ የጉረቤት ሀገሮች ጭምር በመላክ በውጭ ምንዘሬ ግኝት ብሎም በሰፊው የስራ እድል ፈጠራ ላይ የድርሻውን እንደሚወጣ በማሳወቅ በይፋ ኢንዱስትሪው ስራ መጀመሩን አሳውቋል፡፡

ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL

Website- http://www.investinamhara.gov.et/

YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg

WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo

Twitter- https://x.com/amhara_and77292

TikTok- https://www.tiktok.com/@investamhara.regi?_t=8rw4bEMf3hg

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top