የጣና መቀነት የአረንገጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግር ልማት ቀጠና ¨ ይህ ቀጠና በጣና ሐይቅ ዙሪያ የሚገኙ ከፊል የምዕ/ጎጃም ፣ደ/ጎንደርና የማዕከላዊ ጎንደር አካባቢዎችን እና ባሕር ዳር ከተማን የሚያካልል ነው ፡፡ ¨ ይህ ቀጠና ሰፊ የውኃ ሀብት፣ሜዳማ መልካአምድርራዊ ገፅታ፣ተፈጥሮአዊና ታሪካዊ የቱሪስት መስህቦች የሚገኙበት በመሆኑ ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ፣ለእንሰሳትና የዓሳ ሃብት ልማት ዘርፉ ፣ለግብርና ውጤት ማቀነባበሪያ( Agro-processing ) ዘርፉ፣ለቱሪዝም ዘርፉ እንዲሁም ለአገልግሎት (ከተማ ልማትና ቴክኖሎጂ ነክ) የተመረጠ ነው፡፡ ¨ ስለሆነም በቀጠናው የቅድሚያ-ቅድሚያ የሚሰጣቸው ኢንቨስትመንት ዓይነቶች ሆቴልና ቱሪዝም፣ሆርቲካልቸር፣የወተት ሀብት ልማት፣የደሮ እርባታና ስጋ ማቀነባበር ፣የዓሳ ሀብት ልማትና የግብርና ውጤቶች ማቀነባበር ፣የከተሞች ልማት እና ፈጠራና ቴክኖሎጂ ማበልፀግ /ማስፋፋት/ ሥራዎች ናቸው፡፡ ¨ የዚህ ቀጠና ዋነኛ ማዕከል ባህርዳር ሲሆን ወረታ ጨምሮ ሌሎች አዳዲስ ከተሞችን በማልማት በንዑስ የሽግግር ማዕከልነት መጠቀም የሚቻል ይሆናል፡ ለተጨማሪ መረጃ