እንድሪስ አብዱ
የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ
*********
የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በክልሉ በ5 ቀጠናዎች በተደራጀ መልኩ በዞኖችና ከተማ አስተዳድር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያዎች፣ በተመረጡ ሰፊ የኢንቨስትመንት ፍሰት ባለባቸው ወረዳና ከተሞች፣ እንዲሁም ተገምግመው ባለፉና መሬት በተረከቡ፣ ባዶ ቦታ አጥረው በተቀመጡ፣ በክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ ፕሮጀክታቸው ተገምግሞ አልፈው መሬት በወሰዱ/ መሬት ባልተረከቡ፣ ግንባታ አፈፃፀማቸው በዘገዩ፣ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ግንባታ አጠናቀው ወደ ምርት ባልገቡ እና ማነቆዎች ቢፈታላቸው በአጭር ጊዜ ወደ ምርት/ አገልግሎት የሚገቡ፣ በአጋርና ባለድርሻ አካላት ችግሮቻቸው ሊፈታላቸው የሚገቡ የአምራችና ከአምራች ውጭ የሆኑ ሌሎች ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ተለይተው ተገቢ የሆነ ድጋፍና ክትትል ሲደረግላቸው ሰንብቷል።
በሁሉም ቀጠና የነበረው የድጋፍና ክትትል ሁኔታም የቢሮው ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱን ጨምሮ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት የመስክ ማጠቃለያ ውይይትና ግምገማ ተካሂዷል።
በድጋፍ ቡድኖቹ የየቀጠናው ሪፓርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኃላ በተሰጠ የቢሮው አመራሮች ማጠቃለያ የተደረገው አጠቃለያ ድጋፍና ክትትል በየጊዜው እየተሻሻለና በለውጥ ውስጥ ነው በዚህም በሄድንበት ቦታ በሙሉ ችግሮችን ለይተን ባለቤት በመስጠትና መፍትሔ ማመላከታችን ይበል የሚያሰኝ ነው ሲሉ የቢሮው አማካሪ አቶ ባየ አለባቸው ገልፀዋል።
በተያያዘ የቢሮው የኢንቨስትመንት ዘርፍ ምክትል ኃለፊ የሆኑት አቶ ዮሐንስ አማረም በበኩላቸው ካለፉት ጊዚያት አዳጊ የሆነ ክትትልና ድጋፍ ተደርጓል ይሁንና ሁለቱንም የአምራችና ከአምራች ውጭ የሆኑ ሌሎች የሆርቲካልቸር፣ አገልግሎትና ግብርና ዘርፎች እኩል ውጤት ሊያስመዘግብ የመችል ሁለንተናዊ ድጋፍ ልንደግፍ ይገባል ብለዋል።
አቶ ተፈሪ ታረቀኝ የቢሮው የኢንዱስትሪ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊም በሰጡት ሀሳብ የድጋፍ አቅማችን እያደገ መጥቷል ይሁንና በሪፓርቱ እንደቀረበውና እንደተረዳነው የፕሮጀክት አፈፃፀም ጉዳይ አሁንም ቁልፍ ስብራታችን ነው፣ ባዶ ቦታ አጥሮ የያዘ አለ፣ ቦታ ተረክቦ ግንባታ ያልጀመረ አለ፣ ግንባታ ጀምሮ የቆመ አለ፣ ግንባታ አጠናቆ ወደ ምርት ያልገባ አለ፣ ምርት ጀምሮ ያቆመ አለ፣ እነዚህን ማነቆዎቻቸውን ለይተን መፍታት መቻል አለብን፣ በባለሀብቱ ችግር የሆኑት ላይ ደግሞ ተቆራርጠን ወደ እርምጃ መሄድ አለብን ብለዋል።
በመጨረሻም የመስክ የድጋፍና ክትትል አፈፃፀም መድረኩ ላይ የተገኙትና የመድረክ ማጠቃለያ የሰጡት የቢሮ ኋላፊው እንደገለፁት በዚህ ድጋፍ ለቡድኑ መሰረታዊ ተልዕኮዎች ተሰጥተዋል ዋና ዋና ዋናቹም ዞኖችን ክልል ላይ በተሰጠው ኦረንቴሽን መሰረት እቅድ አቅደው ከባለሙያውና ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ አድርገዋል ወይ?፣ የሪፎርም ስራዎች (የተቋም ግንባታና አገልግሎት አሰጣጥ) በተመለከተ ያሉበት ደረጃ፣ የአምራች ኢንዱስትሪና ከአምራች ውጭ ያሉ ሌሎች ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችስ ምን ደረጃ ላይ ናቸው ? ለቀጣይ የተሻለ አፈፃፀምስ ምን እየተሰራ ነው?፣ የኢንሸቲቭ አፈፃፀማቸው (ኢትዮጵያ ታምርትና የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽንስ) ምን ደረጃ ላይ ነው የሚለውን ሁሉን ተግባር ባማከለ መልኩ ደግፎ መፍትሔ ማምጣት ለመስክ ድጋፍ ቡድኑ የተሰጡ ተልዕኮዎች መሆኑን አንስተዋል።
አቶ እንድሪስ አክለው እንደገለፁት ቢሮው ከአበይት ተግባራት እኩል በኢትዮጵያ ታምርትና የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢንሸቲቮች ይመዘናል ያሉት ኃላፊው በቀጣይም አቅምን የሚያሳድግ የተደራጀ ስልጠና በፓኬጅ እንሰጣለን፣ በዚህ ድጋፍ መድረስ አዳጋች የሆኑ ቦታዎችን ሁሉ ደርሰን መደገፋችን የተቋማችን ጥንካሬ ያጎላዋል በቀጣይም ያልደረስንባቸውን ውስን ቦታዎች ልንደርስ ይገባል ብለዋል።
አሁን ሰፊ የአካባቢ ሽፋን ከመድረስ ባሻገር በርካታ ፕሮጀክቶችም ክትትል ተደርጎ ተደግፈዋል፣ ማነቆዎችን ለመፍታት የሚያስችሉ ውይይቶች ከባለድርሻ አካላት ጋር በማድረግ ዞኖችን በድጋፍ በተገኘው ውጤት መመዘኑ ተጠናከሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም አቶ እንድሪስ ከቀጣይ አነፃር ተቋም ግንባታ፣ ካፒታልን መሰረት ያደረገ ኢንቨስትመንት መሳብ፣ ምርታማነትን ማሳደግ፣ ማነቆዎችን መፍታት፣ ኢንሸቲቮች ላይ ማተኮርና የተጀመረውን የድጋፍና ክትትል አግባብ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ አቅጣጫ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።።
ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook
Website-http://www.investinamhara.gov.et/
YouTube-
youtube.com/channel UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg
WhatsApp Channel –https://whatsapp.com/channel/0029Vb769KiHrDZb8EXzee0L
Twitter-https://x.com/amhara_and77292
Telegram Channel -Investinamharahttps://t.me/invmek
Instagram- https://www.instagram.com/investinamhara?igsi=MTJrZzdsdWhrNzViYQ==

