በኮምቦልቻ ከተማ 145 ኢንዱስትሪዎች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ታምርት ክልላዊ የማጠቃለያ መድረክ ዛሬ ይካሄዳል።

ኮምቦልቻ ከተማ 145 ኢንዱስትሪዎች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ታምርት ክልላዊ የማጠቃለያ መድረክ ዛሬ ይካሄዳል።

ኮምቦልቻ፣ግንቦት 30/2018 ዓ.ም (ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ)

በዚህ መድረክ ላይ ለመታደም ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል እና ሌሎችም ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተዋል። ክልላዊ የንቅናቄ ማጠቃለያ መርሐ ግብሩ “ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት” በሚል መሪ መልዕክት ነው የሚካሄደው።

በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን አቅርበው የሚያስተዋውቁበት እና የሚሸጡበት ኤክስፖም ተዘጋጅቷል።

ንቅናቄው አምራቾች ምርታቸውን እንዲያስተዋውቁ፤ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ እና ችግሮቻቸውን ተቀርፈውላቸው የተሻለ እንዲያመርቱ የሚያስችል ነው።

በኤክስፖው 145 ኢንዱስትሪዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

ርእሰ መሥተዳድሩ በቆይታቸው “ኢትዮጵያ ታምርት” ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ኤክስፖን ይከፍታሉ፤ ከባለሀብቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋርም ይወያያሉ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top