***********************************************
ኢኢቢ: የካቲት 11/2017 ዓ.ም (ባህርዳር) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ”ኢትዮጵያ ታምርት፤ እኛም እንሸምት” በሚል መሪ መልዕክት ከከተማ አሥተዳደሩ ባለሃብቶች እና አጋር አካላት ጋር የንቅናቄ የውይይት አድርጓል። አምራቾችም ምርታቸውን ለዕይታ እና ለሽያጭ አቅርበዋል።
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት መርሐ ግብር ያጋጠመውን የምጣኔ ሃብት ስብራት ለመጠገን ታልሞ የተገባበት ነው ብለዋል። ተሞክሮ በመቅሰም ለተከታታይ ዓመታት ንቅናቄ የተደረገበት መኾኑንም ገልጸዋል።
ንቅናቄው በዘርፉ ያለውን ማነቆ በቅንጅት መፍታት እና የአምራች ኢንዱስትሪውን የዘላቂ ልማት ተወዳዳሪነት ማረጋገጥ የትኩረት ነጥቡ ነው ብለዋል። ዘርፉ ለምጣኔ ሃብት መዋቅራዊ ሽግግር አስተዋጽኦ እንዳለውም ገልጸዋል።
ባለፉት ሦስት ዓመታት የተለያዩ ጥያቄዎች እየተፈቱ እና የአምራቾች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱን ኀላፊው ተናግረዋል። በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ በክልሉ 111 አምራች ኢንዱስትሪዎች በአዲስ ማምረት መጀመራቸውን ገልጸዋል። የማምረት አቅምም ከ49 ነጥብ 4 በመቶ ወደ 59 ነጥብ 2 በመቶ ማደጉንም ገልጸዋል። ሸቀጦችን በማቅረብ እና ገበያን በማረጋጋት የኅብረተሰቡ ተጠቃሚነት እያደገ ነው ብለዋል።
“ከ91 ሺህ በላይ ዜጎች በአምራች ኢንዱስትሪዎች የሥራ እድል እንደተፈጠረላቸውም” ገልጸዋል። ከንቅናቄው መጀመር ወዲህ በተሠሩ ጥቂት ሥራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መታየታቸውን ነው የገለጹት።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ ብርሃን ንጉሴ የ”ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” ዓላማ እንደ ሀገር ንቅናቄው ከተጀመረ በኋላ መምሪያው በባለቤትነት ይዞ በየዓመቱ እያስኬደው መኾኑን ተናግረዋል። ዓላማውም ባለሃብቶች እና ባለ ድርሻ አካላት ተገናኝተው በጋራ ሥራዎቻቸው ላይ በመመካከር ችግር ለመቅረፍ እንደኾነ ጠቅሰዋል።
በውይይቱ የተሳተፉት የዩኒክ ፓስታ፣ ማካሮኒ እና ዱቄት ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ ጌጡ ያዩ ፋብሪካቸው በቀን 400 ኩንታል ማካሮኒ የሚያመርት እና ለ400 ሠራተኞች የሥራ ዕድል የፈጠረ መኾኑን ገልጸዋል።
አልፋ የልብስ እና የገላ ሳሙና ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ ብሩክ ታዴ በሁለት ወራት ውስጥ ወደ ሥራ የገባው ፋብሪካቸው ለ60 ሠራተኞች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ገልጸዋል። በቀን እስከ 1 ሺህ ካርቶን እንደሚያመርቱም ተናግረዋል።
በቀጣይ የፈሳሽ ሳሙናን ለማምረት ያቀደው ድርጅታቸው አዲስ አበባ ለመላክ መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል። አሚኮ
ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL
Website- http://www.investinamhara.gov.et/
YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg
WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo
Twitter- https://x.com/amhara_and77292
TikTok- https://www.tiktok.com/@investamhara.regi?_t=8rw4bEMf3hg…

See insights and ads
All reactions:
19Gashaw Awoke – ጋሻው አወቀ, Debark wereda industry and investment office and 17 others