#########################################################
ኢኢቢ የካቲት 12 /2017 ዓ.ም (ባህር ዳር)
‘’ክልሉ በ2022 በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ የተመሰረተ ሆኖ ማየት’’ የሚል ርዕይ ይዞ ወደ ተግባር የገባው የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ከቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች ጋር የግምገማ መድረክ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ም/ቢሮ ኃላፊ እንደገለፁት ባለፉት ስድስት ወራት ብዙ ፈታኝ ሁኔታዎች ቢኖሩም በርካታ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡ ያልተከናወኑ ተግባራትን ለማከናወን በቀሪ ስድስት ወራት በልዩ ትኩረት ተግባራትን መፈጸም እንደሚገባ ሃላፊው ገልፀዋል፡፡
ዝርዝር የቢሮውን የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በቢሮው የዕቅድና በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተራማጅ አገር አማካኝነት ቀርቧል፡፡ ከቀረበው ሪፖርት ለመረዳት እንደተቻለውም ቢሮው ባለፉት ስድስት ወራት 199.3 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 1146 አልሚ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ አውጥተዋል፡፡ ለ34,562 ዜጎችም ቋሚ የስራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡
ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረብ ሊንኮች በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡
Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL
Website- http://www.investinamhara.gov.et/
YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg
WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo
Twitter- https://x.com/amhara_and77292
TikTok- https://www.tiktok.com/@investamhara.regi?_t=8rw4bEMf3hg