92 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገበት የዱቄት ፍብሪካ ተመረቀ።

*******************************************

ኢኢቢ: የካቲት 12/2017 ዓ.ም :ባህርዳር

የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ የተገነባ የዱቄት ፋብሪካን መርቀዋል።

የሥራ ኀላፊዎቹ በራያ ቆቦ ወረዳ አራዱም 08 ቀበሌ ሲገነባ የቆየን ጎሊና የዱቄት ፋብሪካን ነው የመረቁት።

ፋብሪካው 92 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገበት ሲኾን በአራት ወራት ተሠርቶ እንደተጠናቀቀ ተገልጿል። በቀን 400 ኩንታል የማምረት አቅም አለውም ተብሏል።

የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ዱቄት ፋብሪካው በአጭር ጊዜ ተገንብቶ መጠናቀቁ በአካባቢው የተረጋጋ ሰላም መኖሩን ማሳያ ነው ብለዋል።

የክልሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸው 60 በመቶ እንዲጨምር ለማድረግ የክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር የኤሌክትሪክ ኃይል እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች እንዲሟሉ ያደርጋል ብለዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር አካባቢው ለዱቄት ፋብሪካው የሚኾን ግብዓት ለማግኘት አመች እንደኾነ ተናግረዋል።የቆላ መስኖ ስንዴ ማምረት የሚያስችል ጸጋ ያለበት እንደኾነም ገልጸዋል።

በምረቃ መርሀ ግብሩ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ፍስሃ ደሳለኝን ጨምሮ የክልል እና የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL

Website- http://www.investinamhara.gov.et/

YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg

WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo

Twitter- https://x.com/amhara_and77292

TikTok- https://www.tiktok.com/@investamhara.regi?_t=8rw4bEMf3hg

+2

See insights and ads

Boost post

All reactions:

28South Gondar Investment and 27 others

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top