ኢኢቢ: ጥር 13/ 2017 ዓ.ም (ባህርዳር) የኢዱስትሪ ሚኒስቴር የ2017 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀሙን ለክልልና ከተማ አስተዳደር ፣ ተጠሪ ተቋማት፣ ባለ ድርሻ አካላትና የዘርፍ ማህበራት አቅረቦ እየገመገመ ነው ።
የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ያቀረቡት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን አባይ እንደገለፁት መንግስት ለዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት፣ በተሰሩ ቅንጅታዊ ስራዎችና ድጋፎች የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም ከአለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
ዋና ዋና በሆኑ የስራ ማሳያዎች እንደ ውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ተኪ ምርት፣ የአቅም አጠቃቀም፣ የግብዓት አቅርቦትና ሌሎች የዘርፉ ስራዎች ተስፋ ሰጪ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በፋይናስ በአቅም ግንባታ ፣ በመሰረተ ልማትና በምርምር ስኬታማ ስራዎች በመስራቱ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ መቻሉን የገለፀፁት አቶ ጥላሁን የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈፃፀም ከ2016 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ መሆኑን ጠቁመዋል ።
ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL
Website- http://www.investinamhara.gov.et/
YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg
WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo
Twitter- https://x.com/amhara_and77292
TikTok- https://www.tiktok.com/@investamhara.regi?_t=8rw4bEMf3hg…

See insights and ads
All reactions:
12Ermias Mekonnen and 11 others