“የኢንቨስትመንት ውጤታማነት በመሪው አስተሳሰብ ልቀት ይወሰናል”

አቶ አህመድ አሊ

**********************************************************/

ኢኢቢ: የካቲት 14/2017ዓ.ም. :ባህርዳር

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ቦርድ አባላት በዞኑ ባሉ የኢንቨስትመንት ዘርፋ ያሉ ተግዳራቶችና ጥንካሬዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ላይ በብሄረሰብ አስተዳደሩ ያሉ ፀጋወችን የሚያሳይ ሰነድ በኢንቨስትመንት ኮሚቴ ቀርቧል።

የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ አባ ፋሮ እንደገለፁት በዞኑ ያሉ ፀጋዎችን በመለየት የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ዘርፋን ሊቀይር በሚችል መልኩ ፀጋን የመለየት ስራው በተገቢው መሰራቱ ዞኑ በዘርፋ ወደ አዲስ ምእራፍ እየተሻገረ መሆኑን ያመላክታል ብለዋል።

አልሚ ባለሀብቶችን ለልማት ከመጥራት በፊት በዞኑ ያሉ ፀጋዎችን መለየት የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነበር ይሄን ትልቅ ስራ ለማከናወን ወደ ተግባር በመገባቱ የዞናችንን ሀብት በቅጡ ማወቅ ችለናል፣ በቀጣይ በማበልፀግ አልሚዎችን ወደ ዞኑ በመሳብ አመራር መስጠት ይገባልም ብለዋል።

የተገኘውን ሰላም በልማት በማጀብ ኢንድስትሪና ኢንቨስትመንት ዘርፋን ማስተሳሰር እንደሚገባ የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው የኢንቨስትመንት ቦርድ አባላትም ያሉ ፀጋዎችን በመለየት በቅንጅት መስራት እንደሚገባና ፀጋ ያልተለዩባቸውም በአጭር ግዜ ተጠንቶ እንዲቀርብ አሳስበዋል።

ያሉ እምቅ ሀብቶችን በመጠቀም ኢንቨስትመንት ዘርፋን በተገቢው በመምራት አካባቢውን መቀየር እንደሚገባና የኢንቨስትመንት ውጤት በመሪው አስተሳሰብ እድገት ይገለፃል ብለዋል።

በመጨረሻም ዋና አስተዳዳሪው የኢንቨስትመንት መምሪያ ከዚህ በፊት የነበረውን የመረጃ ድርቅና የጨበጣ ስራ ችግር በመሻገር ተጨባጭና መሬት ላይ ባለ ፀጋ ላይ መስራት የሚያስችል የተጠና የፀጋ ልየታ አድርጎ በተደራጀ መንገድ አዘጋጅቶ ማቅረቡ ዞኑ በዘርፋ ያለበትን ችግር በከፍተኛ ሁኔታ የሚፈታ በመሆኑ በዚህ መርሀ ግብር የተሳተፋ ባለሙያወቹንና ተቋሙን አመስግነዋል

የውይይቱ ተሳታፊ የኢንቨስትመንት ቦርድ አባላት በበኩላቸው በዞኑ አመራር ቁርጠኝነት ክትትል እና ድጋፍ ትኩረት የተሰጠበት ዘርፍ መሆኑን ገልፀው አልሚ ባለሀብቶች የውሃ መብራትና መሰል የመሰረተ ልማት ችግሮች ሊቀርፍ በሚችል መልኩ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

የብሄረሰብ አስተዳደሩ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሀላፊ አቶ መሀመድ ይማም እንዳሉት የኢንቨስትመንት ዘርፋን በላቀ ሁኔታ ለመፈፀም ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑና ከአመራር እስከ ማህበረሰቡ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ይገባዋል ብለዋል።

አልሚ ባለሀብቶች የአካባቢውን ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሚታ ሊጠቅም በሚችል መልኩ ሊያለሙ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL

Website- http://www.investinamhara.gov.et/

YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg

WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo

Twitter- https://x.com/amhara_and77292

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top