“ሥራ አቁመው የነበሩ ከ625 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ ተደርጓል”

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል

ኢኢቢ ጥር 13/2017 ዓ.ም (ባህር ዳር)

የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የዕቅድ አፈጻጻም የስትሪንግ ኮሚቴ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ መልዕልት ያስተላለፉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል የኢትዮጵያ ታምርት ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ወደ ሥራ ከገባ ጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሥራ አቁመው የነበሩ ከ625 በላይ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

የአምራች ኢንዲስትሪዎች የማምረት አጠቃቀም 46 በመቶ እንደነበር የገለጹት ሚኒስትሩ ንቅናቄው ከተጀመረ ጀምሮ እስከ አሁን በአማካይ የማምረት አቅም ወደ 61 በመቶ ከፍ ብሏል ነው ያሉት።

ንቅናቄው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ትኩረት እንዲያገኝ እና የዘርፉ ችግሮች ላይ መፍትሔ ለማስቀመጥ እድል መፍጠሩን ነው የተናገሩት።

ተከታታይነት ያላቸው ውይይቶችን በማድረግ ለችግሮቹ የመፍትሔ ባለቤት መኾን በመቻሉ የማምረት አቅም አጠቃቀም፣ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች መተካት፣ በራስ ምርት የመኩራትና የመጠቀም ባሕላችን እየተሻሻለ መጥቷል ብለዋል። በመድረኩም የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ እና ም/ቢሮ ኃላፊው አቶ ተፈሪ ታረቀኝን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL

Website- http://www.investinamhara.gov.et/

YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg

WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo

Twitter- https://x.com/amhara_and77292

TikTok- https://www.tiktok.com/@investamhara.regi?_t=8rw4bEMf3hg

See insights and ads

Boost post

All reactions:

22Tilahun Dejenie and 21 others

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top