ኢኢቢ ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም (ባህር ዳር)
በየደረጃው ለምትገኙ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም በኢትዮጵያና ውጭ በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
የጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመወለዱ ሚስጥር የሰው ልጆችን ከጨለማው ዓለም ነጻ ለማውጣትና የዘለዓለምን ሕይወት ለመስጠት ነው፤ ይህ የጌታችን የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት ማሳያችን እንደሆነ ሁሉ እኛም ሰላምንና አንድነትን የምናረጋግጥበት በዓል ሊሆን ይገባል። በዓሉን ስናከብር ሁላችንም ሰላማችንን በመጠበቅ እንዲሁም የተጀመረውን የክልላችን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ከታለመው ዓላማ ለማድረስ ከመላው የክልላችን ህዝብ ጋር ከምንጊዜውም ጊዜ የበለጠ በአንድነትና በቅንጅት የምንሰራበት ወቅት እንዲሆን እንፈልጋለን። በዓሉ ሲከበርም የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት እና ወንድማማችነትን፣ አብሮነትንና አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ መሆን አለበት ፡፡
በድጋሚ እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ !!!
እንድሪስ አብዱ
የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ
ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL
Website- http://www.investinamhara.gov.et/
YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg
WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo
Twitter- https://x.com/amhara_and77292
TikTok- https://www.tiktok.com/@investamhara.regi?_t=8rw4bEMf3hg