Notice: Function _load_textdomain_just_in_time was called incorrectly. Translation loading for the astra domain was triggered too early. This is usually an indicator for some code in the plugin or theme running too early. Translations should be loaded at the init action or later. Please see Debugging in WordPress for more information. (This message was added in version 6.7.0.) in /data/var/www/vhosts/investinamhara.gov.et/httpdocs/wp-includes/functions.php on line 6260
ዩኒሰን ዘይት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ መጭውን የገና በዓል ታሳቢ በማድረግ የማምረት አቅሙን ማሳደጉን ገለፀ !!!
Deprecated: Function WP_Dependencies->add_data() was called with an argument that is deprecated since version 6.9.0! IE conditional comments are ignored by all supported browsers. in /data/var/www/vhosts/investinamhara.gov.et/httpdocs/wp-includes/functions.php on line 6260

ዩኒሰን ዘይት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ መጭውን የገና በዓል ታሳቢ በማድረግ የማምረት አቅሙን ማሳደጉን ገለፀ !!!

*******************************************

ኢኢቢ: ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም: ባህር ዳር

የዩኒሰን ሆቴል እህት ኩባንያ የሆነውና ከተቋቋመ 3 ዓመት ገደማ የሆነው ዩኒሰን ዘይት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረውን መጭውን የገና በዓል ታሳቢ በማድረግ የማምረት አቅሙን ማሳደጉን የፋብሪካው ጀነራል ማናጀር አቶ አሻግሬ ጌትነት ለአሚኮ ሚዲያ ኮርፖሬሽንና ለክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ገልፀዋል፡፡ ጀነራል ማናጀሩ እንደገለፁት ፋብሪካው ቀደም ሲል በቀን 60,000 ሊትር ዘይት ሲያመርት የቆየ መሆኑን ገልፀው አሁን ላይ በዓሉን ታሳቢ በማድረግ 90,000 ሊትር ዘይት በማምረት ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ እየተደረገ መሆኑንና ያለውን የኑሮ ውድነቱን በማረጋጋት በኩል ፋብሪካው ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አቶ አሻግሬ ጌትነት አብራርተዋል፡፡ ድርጅቱ ከዘይት ምርቱ በተጨማሪ የአኩሪ አተር ተረፈ ምርት ወደ አውሮፓ ገቢያ (ፓኪስታን) ኤክስፖርት በማድረግ የውጭ ምንዛሬ ለሀገሪቱ በማስገኘት በኩል መልካም ጅምር እንቅስቃሴ መኖሩን ከፋብሪካው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ ፋብሪካው ለ250 ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል ፈጥሯል፡፡

ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL

Website- http://www.investinamhara.gov.et/

YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg

WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo

Twitter- https://x.com/amhara_and77292

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top