“መልካም አስተዳደር በተቋማችን በሰራተኞችና አመራሮች መካከልና ብሎም ወደ ተቋማችን ከሚመጡ ባለሀብቶች ጋር ከሚደረግ ቅንና መልካም ግንኙነት ይጀምራል”

የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ

*******************************************

ኢኢቢ: ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም: ባህር ዳር

እንድሪስ አብዱ

የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት በየአመቱ ራሱን የቻለ እቅድ በማዘጋጀት የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ይፈታል፤የእቅድ አፈፃፀም ሪፓርቱንም በየጊዜው ከሰራተኞች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመገምገም ይከታተላል ።

ቢሮው የ2017 ዓ.ም የ5 ወራት የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈፃፀም እና የሪፎርም ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ እና የቀጣይ ወራት እቅድን በተመለከተ ከጠቅላላ የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች ጋር ዛሬ ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ ሌክ አቬኑ ሆቴል ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩም የቢሮው ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ መክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም እንደገለፁት ተቋም ሲገነባ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚያያዙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይተን የእቅዱ አካል አድርገናልና።

መልካም አስተዳድር ከተቋም ግንባታ ይጀምራል፣ መልካም አስተዳደር በተቋማችን በሰራተኞችና አመራሮች ወደ ጎን ወደ ላይና ወደ ታች በሚደረግ ጥሩ ግንኙነት እንዲሁም ወደ ተቋማችን ከሚመጡ ባለሀብቶች ጋር ከሚደረግ ቅንና መልካም ግንኙነት ይጀምራል፣ ሲቀጥል ስራዎቻችን ዲጂታላይዝ ማድረግም አንዱ ቁልፍ የመልካም አስተዳድር መፍቻ በመሆኑ በፍጥነት ወደ ትግበራ መግባት ያስፈልጋል፣ ዲጂታላይዜሽንንም በተግባር መፈፀም ጀምረናል፣ እያጎለበትነው ልንሄድ ይገባል።

አቶ እንድሪስ አክለው ተቋሙ መልካም አስተዳደር

እንዲሰፍንበት ጥረት እያደረግን ነው፣ ይሁንና ሁላችንም ለዚህ ስኬት እውን ቤተሰብ ሁነናል ወይ ብለን ልንጠይቅ ይገባል፣ ትልቁ ስኬት የሚጀምረው ከመልካም ግንኙነት ነው በዚህም የተሰጠንን ተግባርና ሀላፊነት መስራት ቀላል ይሆንልናል ብለዋል። አሁንም ቢሆን የሪፎርም ስራዎቻችን ተጠናክረው ይቀጥላሉ፣ ስራዎቻችን ከሀሜትና ከኋላ ቀር አሰራር ነፃ እንዲሆን ዲጂታላይዜሽን ተግባራዊ ለማድረግ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም እየለማ ይገኛል፣ የፕሮሞሽን ስራችን ቀላልና ተደራሽ የሚያደርግ ዌብሳይት ደግሞ ለምቶ ወደ ትግበራ ገብቷል ብለዋል።

በመቀጠል በአቶ ባየ አለባቸው የቢሮው አማካሪ አማካኝነት የአምስት ወር የሪፎርምና የመልካም አስተዳደር ተግባራት አፈፃፀም ሪፓርት እና የቀጣይ ወራት እቅድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL

Website- http://www.investinamhara.gov.et/

YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg

WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo

Twitter- https://x.com/amhara_and77292

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top