Notice: Function _load_textdomain_just_in_time was called incorrectly. Translation loading for the astra domain was triggered too early. This is usually an indicator for some code in the plugin or theme running too early. Translations should be loaded at the init action or later. Please see Debugging in WordPress for more information. (This message was added in version 6.7.0.) in /data/var/www/vhosts/investinamhara.gov.et/httpdocs/wp-includes/functions.php on line 6260
ከሕዳሴ ግድብ የመነጨው ሃይል በአግባቡ እየተከፋፈለ መሆኑ ተገለጸ
Deprecated: Function WP_Dependencies->add_data() was called with an argument that is deprecated since version 6.9.0! IE conditional comments are ignored by all supported browsers. in /data/var/www/vhosts/investinamhara.gov.et/httpdocs/wp-includes/functions.php on line 6260

ከሕዳሴ ግድብ የመነጨው ሃይል በአግባቡ እየተከፋፈለ መሆኑ ተገለጸ

***************************************

ኢኢቢ: ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ባህርዳር) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የሆለታ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመነጨውን ሃይል በአግባቡ እያከፋፈለ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የጣቢያው ሃላፊ አቶ ጥላሁን አዘዘው እንደገለጹት÷የማከፋፈያ ጣቢያው እያንዳንዳቸው 750 ሜጋ ቮልት አምፔር አቅም ያላቸው ሰባት ትራንስፎርመሮች አሉት፡፡

ጣቢያው በአሁኑ ወቅት ከሕዳሴ ግድብ በአራት ተርባይን እየመነጨ ያለውን 1 ሺህ 500 ሜጋ ዋት ሃይል ከዴዴሳ ማከፋፈያ ጣቢያ ተቀብሎ ወደ ተለያዩ ማከፋፈያ ጣቢያዎች በማሰራጨት ከግሪዱ ጋር እንደሚያገናኝ ገልጸዋል፡፡

ጣቢያው ከደዴሳ በባለ 500 ኪሎ ቮልት አራት መስመሮች ሃይል ተቀብሎ በ400 ኪሎ ቮልት በጥምር መስመር ለሱሉልታ፣ ሰበታና ገላን ማከፋፈያ ጣቢያዎች ሃይል እያቀረበ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በ3 ባለ 33 ኪሎ ቮልትና በ6 ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ለተለያዩ አካባቢዎች ሃይል እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን÷በባለ 132 ኪሎ ቮልት መስመር ደግሞ ለሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሃይል እየሰጠ ነው ብለዋል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀሪ ተርባይኖች ወደ ሥራ ሲገቡ የመነጨውን ሃይል በሙሉ ተቀብሎ በአግባቡ ለማከፋፈል ዝግጁ መሆኑን አቶ ጥላሁን አንስተዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ ተርባይኖች 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም እንዳላቸው መጠቆሙንም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል መረጃ አመልክቷል፡፡ ኤፍ ቢ ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top