Notice: Function _load_textdomain_just_in_time was called incorrectly. Translation loading for the astra domain was triggered too early. This is usually an indicator for some code in the plugin or theme running too early. Translations should be loaded at the init action or later. Please see Debugging in WordPress for more information. (This message was added in version 6.7.0.) in /data/var/www/vhosts/investinamhara.gov.et/httpdocs/wp-includes/functions.php on line 6260
በአማራ ክልል 163 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ ተሰጠ
Deprecated: Function WP_Dependencies->add_data() was called with an argument that is deprecated since version 6.9.0! IE conditional comments are ignored by all supported browsers. in /data/var/www/vhosts/investinamhara.gov.et/httpdocs/wp-includes/functions.php on line 6260

በአማራ ክልል 163 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ ተሰጠ

***************************************

ኢኢቢ: ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ባህርዳር ) ከሐምሌ 1 ቀን 2016 ጀምሮ በአማራ ክልል 163 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 940 አልሚዎች ፈቃድ መሰጠቱን የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ፈቃድ የተሰጣቸው አልሚዎች ወደ ስራ ሲገቡ ለ20 ሺህ 368 ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ቢሮው ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

አልሚዎቹ በአግሮፕሮሰሲንግ፣ ጨርቃጨርቅ፣ ኬሚካል፣ ኮንስትራክሽን፣ እንጨትና ብረታብረት፣ ቱሪዝም፣ አበባ ልማት፣ ግብርና እና ሪልስቴትን ጨምሮ በሌሎች መስኮች እንደሚሰማሩ ቢሮው አብራርቷል፡፡

በክልሉ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የኢኮኖሚ ድርሻም 8 ነጥብ 5 መሆኑን ነው ቢሮው ያስታወቀው፡፡

የኢንቨስትመንት ፍሰቱ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ62 ቢሊየን ብር ጭማሪ ማሳየቱም ተጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል 62 አዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ምርት መግባታቸውን እና ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ49 ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል፡፡ ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው

See insights and ads

Boost post

All reactions:

13Gashaw Awoke – ጋሻው አወቀ and 12 others

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top