﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌﹌
ማዕድን ከሚሰጠው አገልግሎት፣ ዋጋ እና ሌሎች መስፈርቶች በተለያዬ አይነት መልኩ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሀ. የከበረ ማዕድን
የከበረ ማዕድን ማለት እንደ ፕላቲኒዬም ወርቅና ብር የመሰለ የከበረ ብረት ነክ ማዕድን ወይም እንደ አልማዝ፣ ሩቢ፣ ኤመራልድ፣ ሳፋዬር ከከበረ ድንጋይ የተመረተ ሲሆን ሌሎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመመሪያ የከበረ ተብለው የሚሰየሙ ማናቸውንም ሌሎች ማዕድናትን ይጨምራል፡፡
ለ. በከፊል የከበረ ማዕድን
በከፊል የከበረ ማዕድን ማለት ለማስዋቢያነት፣ የሚውል ወጥ ወይም በተፈጥሯዊ አንድነት የተጣመረ እንደ ሮዶላይት፣ ኦሊቪን፣ ጃዲያትና ላዙራይት የመሳሰሉትን ማዕድናት የያዘ ሲሆን የከበሩ ማዕድናትን ሳይጨምር በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመመሪያ በከፊል የከበሩ ተብለው የሚሰየሙ ማናቸውንም ሌሎች ማዕድናትን ይጨምራል፡፡
ሐ. ብረት ነክ ማዕድን
ብረት ነክ ማዕድን ማለት እንደ ብረት፣ መዳብ፣ነሃስ፣እርሳስ፣ክሮማይት፣ ኒኬል፣ ታንታለም እና ማንጋኒስ የመሳሰሉት ማዕድናት ናቸው፡፡ ከበሩና በከፊል የከበሩ ማዕድናትን ሳይጨምር በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመመሪያ በከፊል የከበሩ ተብለው የሚሰየሙ ማናቸውንም ሌሎች ማዕድናትን ይጨምራል፡፡
መ. የኢንዱስትሪ ማዕድን
የኢንዱስትሪ ማዕድናት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለኢንዱስትሪዎች ከግብዓት እስከ ምርት የሚያገለግሉ እንደ ካኦሊን፣ቤንቶናይት፣ ኳርትዝ፣ የድንጋይ ከሰል፣ ላይምስቶን፣ ፖታሽ ፣ጂፕሰም፣ ፑሚስ፣ የሸክላ አፈርና ግራፋይት የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ሠ. የግንባታ ማዕድናት
የግንባታ ማዕድናት ማናቸውም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለኮንስትራክሽን በግብዓትነት የሚያገልግል እንደ ዕምነበረድ፣ ግራናይት፣ ላይምስቶን ፣ ባዛልት፣ አሸዋ፣ ጠጠር፣ ኢግኒምብራይትና የሸክል አፈር የመሳሳሉትን ሲሆን ሌሎች በመመሪያ የሚሰየሙ ማዕድናትን ይጨምራል፡፡
ማዕድን አዲስ የንጋት ተስፋ ለክልላችን!!