**************************************************
ኢኢቢ: ታህሳስ 17/2017: ባህርዳር
በከተማ አስተዳድሩ በ01ፍላቂት ነዋሪ አቶ ሸጋው አስናቀ በተባሉ ባለሀብት የተገነባው የሚስማር ፍብሪካ ስራውን በማጠናቀቅ ወደ ስራ ገብቶ ከ5 ቁጥር ጀምሮ እስከ 15 ቁጥር ሚስማሮችን እያመረተ ይገኛል ።
የወረዳው ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመሆን በከተማ አሰተዳደሩ በግል ባለሀብቶች እየተሰሩ ካሉ የልማት ስራዎች መካከል የሸጋው አስናቀ የሚስማር ማምረቻን እና የመስፍን አለምየ ሞቴልን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም በአብዛኛው እየተሰሩ ያሉ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በጥሩ ደረጃ እየሄዱ መሆኑን የመስክ ምልከታ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
ስራ የጀመረው ሚስማር ማምረቻ ወደ ስራ ለመግባት በሂደት ላይ የሚገኘው ሞቴል የአካባቢውን የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱና ለበርካታ ወጣት የስራድል እንደሚፈጥሩ ተስፋ የተጣለባቸው እንደሆኑ የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
የወረዳው ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገብረኪዳን አጋዥ እንደገለጹት በወረዳውና በፍላቂት ገረገራ ከተማ አስተዳደር ከ65 በላይ ባለሐብቶች መዋዕለ ነዋያቸውን አፍስሰው በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሰማርተው እንደሚገኙ ተናግረዋል ።
የከተማችን ባለሐብቶች አዲስ ነገር ይዘው ከተማችን ለማሳደግና ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ይዘው የሚመጡ ባለሐብቶችን እያመሰገንን ማድረግ የሚገባንን ድጋፍና እንክብካቤ እናደርጋለን ። ሌሎች ባለሐብቶች ይህንን መልካም መፈለግ መከተል እንደሚገባቸው ገልጸዋል ።
ወረዳው እና ከተማ አስተዳድሩ የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ያሉት ሰለሆነ ባለሐብቶች በሚያዋጣቸውና በሚመርጡት የኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲያለሙ ጥሪ አቅርበዋል። መረጃው የመቄት ኮሚኒኬሽን ነው።





See insights and ads
All reactions:
27ሀራ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት, ሞላ ደሱ መኮነን and 25 others