በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነባው የደሴ ዱቄት እና ዳቦ ፋብሪካ ሥራ ጀመረ!!!

ኢኢቢ ታህሳስ 17/ 2017 ዓ.ም (ባህር ዳር)

የደሴ ዱቄት እና ዳቦ ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ ሰለሞን መኮንን ፋብሪካው በቀን 300 ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም እንዳለው ገልጸው በዛሬው ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ከ5 ሺህ በላይ ዳቦ አቅርቧል ነው ያሉት።

በቀጣይም በከተማዋ በሚገኙ በአምስቱም ክፍለ ከተሞች ከ30 በላይ ማዕከላትን በማቋቋም ዱቄት እና ዳቦ የሚያሰራጭ ይሆናል ነው ያሉት።

የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ከተማ አሥተዳደሩ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ በመመደብ የሰው ኀይል እና ግብአትን በማሟላት ዱቄት እና ዳቦ በተመጣጣኝ ዋጋ የማቅረቡ ሥራ በሙሉ አቅም ተጀምሯል ብለዋል። ፋብሪካው በተሟላ ኹኔታ ሥራ እንዳይጀምር እንቅፋት የነበሩት የጄኔሬተር እና የመብራት ችግሮች መፈታታቸውን ተናግረዋል። የፋብሪካው ሥራ መጀመር የኑሮ ውድነቱን ለማቃለል የራሱ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ያሉት ከንቲባው ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL

Website- http://www.investinamhara.gov.et/

YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg

WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo

Twitter- https://x.com/amhara_and77292

TikTok- https://www.tiktok.com/@investamhara.regi?_t=8rw4bEMf3hg

See insights and ads

Boost post

All reactions:

77

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top