ውቢቷ ከተማ #እንጅባራ!!!

ኑ ኢንቨስት ያድርጉ!!

===========+============

ኢኢቢ: ታኅሳስ 17/2017 ዓ.ም ባህርዳር

እንጅባራ ከተማ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ካሉ የብሔረሰብ ዞን ከተሞች ውስጥ አንዷ ስትሆን መንግስት ለከተሞች ልዩ ትኩረት በመስጠት በ1996 ዓ.ም የከተሞች አዋጅ ቁጥር 91/96 መሠረት በሁለት የከተማ ቀበሌ እና በአንድ የገጠር ቀበሌ በመዋቀር 3 ቀበሌዎችን አቅፋ የከተማ አስተዳደር ማዕረግ ያገኘች ስትሆን ከነሐሴ 2009 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በ5 የከተማ ቀበሌዎች የተዋቀረችና በ5 የገጠር ቀበሌዎች በመዋቀር በርካታ የህዝብ ፍሰት ያላት በፈጣን የእድገት ጎዳና ላይ ያለች ከተማ ናት።

እንጅባራ ከተማ የከተማዋን እድገት ከሚያፋጥኑ ሁኔታዎች አንዱ የሆነውን ኢንቨስትመንትን ስንመለከት የኢንቨስትመንት ፍሰቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የአሁኗ ምርጧና ውቢቷ ከተማ እንጅባራ የሚል ስያሜ ሊያሰጣት ችሏል። በመሆኑም እንጅባራ ለኢንቨስትመንት ያላት ምቹ ሁኔታ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ መሬት በምደባ መሠጠቱ፣ የተሻለ መሠረተ ልማት አቅርቦት መኖሩ፣ አስተማማኝ ሰላም መኖሩ፣ የሰለጠነ የሰው ሀይል በሚፈለገው የትምህርት ዝግጅት መኖሩ፣ ምቹና ለኑሮ ተስማሚ የአየር ፀባይ ያላት፣ በቂ የፋይናንስ አቅርቦት መኖሩ፣ ህዝቡ እንግዳ ተቀባይ በመሆኑ የኮንፈረስ ከተማ መሆኗ፣ ለዘርፉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ በመሆኑ ማለትም ከጉምሩክ ቀረፅ ነፃ የካፒታልና የግንባታ እቃዎች የተሽከርካሪና የገቢ ግብር የእፎይታ ጊዜ መስጠቱ፣ እንዲሁም በቂ የኢንቨስትመንት አማራጮች ማለትም

✔ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች ማምረት፣ በጨርቃጨረቅ፣ ቆዳና አልባሳት ማምረት፣ በኬሚካልና የኬሚካል ውጤቶች ማምረት፣ የግንባታ ግብዓት ማምረት እንዲሁም

✔በግብርናው ዘርፍና በአገልግሎት ዘርፍ ለመሠማራት የምትፈልጉ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችም ሆነ በውጭ ሀገር የምትኖሩ ዲያስፖራዎች በውቢቷ እንጅባራ መጥተው ኢንቨስት ያድርጉ አዲናስ ብለን ለመቀበል ዝግጁ ነን።

“እንጅባራ የኢንቨስትመንት ከተማ”

ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL

Website- http://www.investinamhara.gov.et/

YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg

WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo

Twitter- https://x.com/amhara_and77292

TikTok- https://www.tiktok.com/@investamhara.regi?_t=8rw4bEMf3hg

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top