ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ከ310 ሺህ ቶን በላይ ሲሚንቶ ለገበያ አቀረበ !

************************************

ኢኢቢ፡ ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም፡ ባህርዳር

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ ተመርቆ ሥራ የጀመረው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ እስከ አሁን ከ310 ሺህ ቶን በላይ ሲሚንቶ ለገበያ አቀረበ፡፡

ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ ወደ ምርት ሲገባ በቀን 15 ሺህ ቶን (150 ሺህ ኩንታል) ሲሚንቶ የማምረት አቅም እንዳለውም ለፋና ዲጂታል አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በከፊል ወደ ሥራ የገባው ፋብሪካው በቀን እስከ 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ ለገበያ እያቀረበ መሆኑን እና ሥራ ከጀመረ አንስቶ ከ310 ሺህ ቶን በላይ ሲሚንቶ ለገበያ ማቅረብ መቻሉን ነው የገለጸው፡፡

ፋብሪካው ገበያውን መቀላቀሉን ተከትሎም የአንድ ኩንታል ሲሚንቶ ዋጋ ከነበረበት ወደ 1 ሺህ 190 ብር ዝቅ ማለቱን እና ገበያው ላይም የአቅርቦት እጥረት አለመኖሩ ተመላክቷል፡፡

በአጠቃላይ ፋብሪካው ለ1 ሺህ 138 ወገኖች ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠሩም ነው የተገለጸው፡፡

ፋብሪካው መስከረም 18 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ ሥራ ሲጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)÷ ይህ ሜጋ ፕሮጀክት የመንግሥታችን በፍጥነት፣ በግዝፈት እና በንፅህና የመገንባት ጽኑ አቋም ማሳያ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡

እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መሠረተ-ልማቶችን በፍጥነት እና በብቃት አጠናቅቆ ዝግጁ የማድረግ ተምሳሌት መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ ተመሳሳይ ፋብሪካዎች ተደምረው የሚያመርቱትን 50 ከመቶ የሚያመርት እንደሆነም መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ amhara communication

‹‹ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት››

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL

Website- http://www.investinamhara.gov.et/

YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg

WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo

Twitter- https://x.com/amhara_and77292

TikTok- https://www.tiktok.com/@investamhara.regi?_t=8rw4bEMf3hg

May be an image of oil refinery and the Panama Canal

See insights and ads

Boost post

All reactions:

3030

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top