ኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው ሂፋም ሰኢድ አሊ ከረጢት ማምረቻ ፋብሪካ ውጤታማ እንቅስቃሴ እያደረገ እንዳለ ተገለጸ!

************************************

ኢኢቢ፡ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም፡ ባህር ዳር

የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ ዛሬ ታህሳስ 12 ቀን 2017 አ.ም ሂፋም ሰኢድ አሊ ከረጢት ማምረቻ ፋብሪካ የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ ፣ በጉብኝቱም የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድ አሚን የሱፍ፣ የኮምቦልቻ ከተማ ኢንዱስትሪና ኢንቨትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሁሴን ሙሄ ይመር እና በኢትዩጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ቅርጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ ተገኝተው የፋብሪካውን እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት በመገኘት ማብራሪያ የሰጡት የፋብሪካው ባለቤት አቶ ሰይድ አሊ እንደገለጹት ፋብሪካው በሁለት ፈረቃ 24 ሰአት እየሰራ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ፋብሪካቸው ለ448 ቋሚና ለ52 ጊዚያዊ ሰራተኞች የስራ እድል በመፍጠር እየስራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ፋብሪካው ለአምራች ኢንዱስትሪውና ለግብርናው ዘርፍ በግብአትነት የሚያገለግሉ ከረጢቶችን በማምረት በክልላችን ብሎም በሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት ሚናውን እየተወጣ መሆኑን ጠቅሰው አሁን ላይ ግን ከፋብሪካው አቅም ማደግ ጋር ተያይዞ ከማሽኖች ብዛት፤ ከጥሬ እቃና ምርት ማስቀመጫ፤ ከተሸከርካሪዎች ጭነትና ከኢንዱስትሪ አካባቢ አንክብካቤና አረንጓዴ ልማት አንጻር እንዲሁም ስራውን በተገቢው ስታንዳርድ ማለትም ፕላንትና ማሽን ላይአውት መሰረት ሰርቶ ውጤታማ ከመሆን አንጻር ፋብሪካው ከፍተኛ የሆነ የመስሪያ ቦታ ጥበት እንዳለበት በጉብኝቱ ወቅት ለተገኙት የከተማውና የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች ጥያቄ አቅርበዋል።

በመጨረሻም የቢሮው ሃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱና የከተማው አመራሮች በጉብኝቱና በፋብሪካው የስራ እንቅስቃሴ እንደተደሰቱ ገልጸው ቢሮውም ሆነ ከተማ አስተደደሩ አስፈላጊውን ጥያቄ ወስዶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት በማድረግና አቅጣጫ በመስጠት ባለሀብቱ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ልፀዋል።

በመጨረሻም የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳድር አመራሮችና የፋብሪካው ባለሀብት የቢሮውና ክልሉ አመራሮችና ለከተማ አስተዳደሩ የአምራች ኢንዱስትሪ እድገትና ለከተማ አስተዳደሩ ኢንቨስትመንቱ ፍስት ማደግ በአካል በመገኘት ፕሮጀክረቶችን ስለጎበኙና በቀጣይ ደግሞ ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ስለገቡልን እናመሰግናለን ሲሉ የመምሪያው ኃላፊ አቶ ሁሴን ምስጋና አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL

Website- http://www.investinamhara.gov.et/

YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg

WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo

Twitter- https://x.com/amhara_and77292

TikTok- https://www.tiktok.com/@investamhara.regi?_t=8rw4bEMf3hg

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top