የተቀናጁ አግሮ-ኢንዱስትሪያል ፓርኮች በኢትዮጵያ (OS-IAIP) ፕሮጀክት ዋና አላማ በተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የጥራት መሰረተ ልማት እንዲኖር ማድረግ ነው

***************************************

ኢኢቢ: ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም 2ተኛው የፕሮጀክት አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ በተካሄደበት ወቅት የተቀናጁ አግሮ-ኢንዱስትሪያል ፓርኮች በኢትዮጵያ (OS-IAIP) ፕሮጀክት ዋና አላማ በፓርኮች ውስጥ የጥራት መሰረተ ልማት እንዲኖር ማድረግ ነው ያሉት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተቀናጁ አግሮ-ኢንዱስትሪያል ፓርኮች በኢትዮጵያ (OS-IAIP) ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ሄኖክ አበበ በፓርኮች ውስጥ የጥራት መሰረተ ልማትን ለማምጣት የምግብ ጥራት ፍተሻ ቤተ ሙከራዎችን ማደራጀት ላይ ተኩረቱን እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

የታቀደውን ለማሳካትም በአራት ዋና ተግባራት ላይ ማለትም በአግሮ ፓርኮች እና አካባቢው ላይ ያሉ የግብርና ምርቶች የጥራት ደረጃቸውን ጠብቀው ወደ ፓርኮቹ እንዲገቡ የማድረግ፣ የሚመረቱ ምርቶች ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲወጡ ለማድረግ የላቦራቶሪ ግንባታ ማከናወን ፣ የልቀት ማዕከላትን ማደራጀት እና የጥራት መሰረተ ልማት ላይ አትኩረው ለሚሰሩ ባለሃብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ የማድረግ ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራም አቶ ሄኖም ገልፀዋል።

የፕሮጀክቱ ዝግጅት ምዕራፍ ተጠናቆ ወደ ተግባር በተሻገረባቸው የሁለት ወራት ተኩል ጊዜ ውስጥም የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች፣ የልምድ ልውውጦች ፣ለስራው መሳካት መደላድልን የሚፈጥሩ አደረጃጀቶችን የመፍጠርና በአስፈላጊው የሰው ሃይል የማሟላት እንዲሁም አስፈላጊ ግብአቶችን ግዢ የመፈፀም ስራዎች መሰራታቸውንም ማናጀሩ አክለዋል።

#ኢትዮጵያ ታምርት #እኛም_እንሸምት እኛም እንሸምት!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL

Website- http://www.investinamhara.gov.et/

YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg

WhatsApp- https://chat.whatsapp.com/C7sUyLeKQ5D9C4kLK4Uizo

Twitter- https://x.com/amhara_and77292

TikTok- https://www.tiktok.com/@investamhara.regi?_t=8rw4bEMf3hg

See insights and ads

Boost post

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top