የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ በሩብ ዓመቱ 55 ገደማ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን መርምሮ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) ተናገሩ፡፡

የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ በሩብ ዓመቱ 55 ገደማ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን መርምሮ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) ተናገሩ፡፡

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል፡፡

ከክልል እና ከዞን የተውጣጡ የዘርፉ መሪዎች በተገኙበት የሩብ ዓመቱን ዕቅድ አፈጻጸምን የገመገመው ቢሮው በችግር ውስጥም ኾኖ የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡን አስታውቋል፡፡

የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ ባለፉት ሦስት ወራት በአምራቹ እና ኢንዱስትሪው ዘርፍ ለተሰማሩ 113 ባለሃብቶች ከ870 ሄክታር በላይ መሬት ተሰጥቶ ወደ ሥራ ገብተዋል ነው ያሉት፡፡

ኀላፊው አዳዲስ ኢንቨስተሮች ወደ ክልሉ እንዲመጡ ጥረት ተደርጓልም ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄም ውጤታማ ለውጥ ማምጣቱን ናግረዋል፡፡

ነባር ኢንቨስተሮችን በቅርበት ከማገዝ እና ከመደገፍ ባሻገር አዳዲስ ባለሃብቶችም ወደ ክልሉ እንዲመጡ ተሠርቷል ያሉት ኀላፊው በኢንቨስተሮች ቁጥር ብቻ ሳይኾን በካፒታል እና በተሻሻሉ ቴክኖሎጅዎችም ለውጥ ታይቷል ብለዋል፡፡

በቀጣይም ጥንካሬዎችን አስቀጥሎ እና ውስንነቶችን አርሞ ለመሄድ የውይይት መድረኩ አስፈላጊ እንደነበር አንስተዋል፡፡

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) ኢንቨስትመንት የሀገር ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት አቅም ነው ብለዋል፡፡

የሀገር ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት በኢንቨስትመንት አቅም እንደሚቃኝም ዶክተር አሕመዲን ሙሐመድ አስገንዝበዋል፡፡

ምንም እኳን ክልሉ ባለፉት ሦስት ወራት በግጭት ውስጥ ቢያሳልፍም የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ዘርፉ በችግር ውስጥም ኾኖ ለውጥ ማሳየት ችሏል ነው ያሉት፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት የቻለ እንደነበርም አንስተዋል፡፡

የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ ባለፉት ሦስት ወራት ከ200 በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን መመርመሩን ያነሱት ዶክተር አሕመዲን ሙሐመድ የፀደቁት ግን 55 ገደማ ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡

ይህም የሚቀርቡ በርካታ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መሥፈርቱን የማያሟሉ መኾናቸውን ያሳያሉ ብለዋል፡፡

ችግሩ ደግሞ ወደ ታች ያለው የኢንቨስትመንት ቦርድ ፕሮጀክቶችን በአግባቡ መርምሮ እንደማይልክ ያሳያል ነው ያሉት፡፡

በአጠቃላይ በክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ ከጸደቁ 392 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች 206 የሚኾኑት መሬት እንዳልተረከቡ ገልጸዋል፡፡

ዶክተር አሕመዲን ተቀራርቦ እና ተናብቦ በመሥራት በኩል ያሉ ውስንነቶችን ማረም ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

በተለይም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከአልሚ ባለሃብቶች ጋር በነበሩ ውይይቶች የተነሱ ችግሮችን መቅረፍ እና ባለሃብቶችን መሳብ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይም ዘረፉ የተጣለበትን ክልላዊ ኀላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ አሠራርን ማዘመን፣ ኀላፊነትን መወጣት፣ ውጤት ማስመዝገብ እና አገልግሎት አሰጣጥን በዕቅድ መምራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

አሚኮ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top