በባለፉት 5 አመታት በኮቪድና ጦርነት ዉስጥም ሆነን በርካታ ባለሀብቶች ወደ ክልሉ መጥተዉ ኢንቨስት አድርገዋል፡፡ የክልሉን ዘላቂ ልማት የሚያረጋግጡ ግዙፍ ኢንቨስትመንቶች እየገነባን እንገኛለን፡፡

በባለፉት 5 አመታት በኮቪድና ጦርነት ዉስጥም ሆነን በርካታ ባለሀብቶች ወደ ክልሉ መጥተዉ ኢንቨስት አድርገዋል፡፡ የክልሉን ዘላቂ ልማት የሚያረጋግጡ ግዙፍ ኢንቨስትመንቶች እየገነባን እንገኛለን፡፡

**************************************************

ጥቅምት 09/2017 ዓ.ም: ኢኢቢ (ባህር ዳር)

የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ እያካሄደ በሚገኘው የ1ኛ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ባለፉት ሶስት ወራት የተከናወኑ አበይት ተግባራትና በመስክ ድጋፍ የተገኙ ተጨባጭ ግኝቶች ለተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን፣ ባለፈው ሩብ አመት ከዋና ዋና ተግባራት አንፃር አፈፃፀሙ ሲታይ፣ ባለፈው ሩብ አመት አሰራርን ከማዘመን አንፃር ዌብሳይት የማስለማት ስራ ጥሩ ደረጃ መድረሱን፣ የኢንቨስትመንት ኢንፎርሜማኔጅመንት የሚያ

18 ጽ/ቤቶችን ኔት ወርክ የማስጀመር ስራ ተሰርታል፣ 130.47 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ለ 512 አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ፈቃድ ተሰጥቷል። ከመሬት አቅርቦት አኳያ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ 420.3 ሄክታር መሬት በሳይት ፕላን በማመላከት፣ 177.2ሄክታር መሬት ከ3ኛ ወገን ነፃ በማድረግ በሩብ አመቱ ተገምግመው ካለፋት 145 ፕሮጀክቶች ለ40 ፕሮጀክቶች 79.96 ሄክታር መሬት ማስተላለፍ ተችሏል። ከአምራች ኢንዱስትሪ ውጭ ላሉ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ደግሞ 30,883 ሄክታር መሬት በሳይት ፕላን በመለየት፣ 18, 304.2ሄክታር ከሶስተኛ ወገን ነፃ በማድረግ ተገምግመው ላለፈ ሁሉም 43 ፕሮጀክቶች 790. 78 ሄክታር መሬት ማቅረብ ተችሏል። ከ6.7 ቢሊዮን ብር በላይም የሊዝ ፋይናንስ የፕሮጀክት ፋይናንስና የስራ ማስኬጃ ድጋፍም ማቅረብ ተችሏል። በተደረገው ድጋፍም 25 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት ገብተዋል። ሌሎች ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በተለያዩ ጊዚያት ጉዳት ከደረሰባቸው የሆርቲካርቸር የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ውስጥ ጣና ፍሎራ፤ባህርዳር ፍሬሽ ፍሩትና ቆጋ ቬጅና ታል ፍላዎር አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ቀማድረግ ወደ ስራቸው መመለስ ችለዋል፡፡ በተለያየ ጊዜም ቦታ ወስደው ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ባልገቡ እና ለታለመለት ዓላማ ባላዋሉ ፕሮጀክቶች ላይም ክትትል በማድረግ በ 59ኙ ላይ የተለያዩ እርምጃዎች ተወስዷል።

በኢንዱስትሪዎች መካከል በተፈጠረው ትስስርም ከ50,981 ቶን በላይ ግብአት ቀርቧል። ከውጤት አንፃር ሩብ አመቱን ስንገመግም በአምራች ዘርፉ ኤክስፓርት/ ላኪ ኢንዱስትሪ ቁጥር 10 በማድረስ 20,772.2 የምርት መጠን በቶን በመላክ 20 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት ተችሏል። በተመሳሳይ በሆርቲካልቸር ዘርፍ 546.2 ቶን ምርት በመላክ ምርት መጠን በቶን 3.19 ሚሊዮን ዶላር ማገኝት ተችሏል ። በተኪ ምርትም 90 አምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርት እንዲያመርቱ በማድረግ በገንዘብ ሲተመን 77.4ሚሊዮን ዶላር የሚገመት 94,787 ቶን ምርት በማምረት የውጭ ምንዛሬን ማዳን ተችሏል። ከስራ እድል አንፃርም በሩብ አመቱ ለ 6,346 ዜጎችን የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ2,560 ዜጐች ስራ መፍጠር ተችሏል።

በአጠቃላይ በዚህ ሩብ አመት የሚፈለገውን ያክል ቅንጅታዊ አሰራር የኤሌከልትሪክ ሀይልና የመሰረተ ልማት አቅርቦት፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የግብአትና የለማ መሬት አቅርቦት፣ መሬት የወሰዱ ባለሀብቶች ፕሮጀክት አፈፃፀም አዝጋሚነት፣ ደካማ የድጋፍና ክትትል ውስንነት፣ የፕሮጀክት ጥራት ፣ የሰላም እጦት ወዘተ የዘርፉ ተግዳሮቶች በመሆናቸው በአንዳንድ ወሳኝ ተግባራት የተቀመጠውን ግብ ማሳካት አልተቻለም፣ ይሁንና በባለፉት 5 አመታት በኮቪድና ጦርነት ዉስጥም ሆነን በርካታ ባለሀብቶች ወደ ክልሉ መጥተዉ ኢንቨስት አድርገዋል፡፡ የክልሉን ዘላቂ ልማት የሚያረጋግጡ ግዙፍ ኢንቨስተሮችን እየገነባን እንገኛለን፡፡ ባለፈው በጀት አመትም ውጤት ማስመዝገብ ችለናል። በሚደረገው የአንደኛ ሩብ አመትና የ100 ቀናት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ግልፅ ግምገማና ውይይት በማድረግ በቀሪዎቹ የትግበራ ወራት የተሻለ ስራ እንደ ቢሮ ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል።

1 thought on “በባለፉት 5 አመታት በኮቪድና ጦርነት ዉስጥም ሆነን በርካታ ባለሀብቶች ወደ ክልሉ መጥተዉ ኢንቨስት አድርገዋል፡፡ የክልሉን ዘላቂ ልማት የሚያረጋግጡ ግዙፍ ኢንቨስትመንቶች እየገነባን እንገኛለን፡፡”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top