ቢሮው አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን፣በቅንጅታዊ አሰራር አቅርቦትን በማሻሻል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሰራ እንደሆነ አሰታወቀ!

***************************************************
ጥቅምት 09/2017 ዓ.ም: ኢኢቢ (ባህር ዳር)
የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የዞን መምሪያ ሀላፊዎች፣ የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቡድን መሪዎች ፣የእቅድ ባለሙያዎች፣ የፓርክ ጽ/ቤት ሀላፊዎች እንዲሁም የቢሮው ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት በ2017 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም እንዲሁም በ100 ቀን እቅድ አፈፀፀም ዙሪያ ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል ።
በግምገማ መድረኩ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊና የእለቱ የክብር እንግዳ ክቡር ዶ/ር አህመዲን መሀመድ፣ የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ክቡር አቶ እንድሪስ አብዱን ጨምሮ የቢሮው ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች፣ ሁሉም የማኔጅመንት አባላትና የአብክመ የኢንዱስትሪ ፓርክ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የቢሮ ኃላፊው የእለቱን የክብር እንግዳ ግምገማውን በመክፈቻ ንግግር እንዲከፍቱ ጋብዘው ውይይቱ ተጀምሯል ።
አቶ እንድሪስ እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ባደረጉበት ወቅት በበጀት አመቱ መጀመሪያ ወቅት በተሰጠው የእቅድ ኦረንቴሽን ወቅት ሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች አገልግሎት አሰጣጣችንና የአሰራር ስርአታችን ከማዘመንና ከማሻሻል ፣ የተሳለጠና የላቀ አገልግሎት ከመስጠት አንፃር ባለፈው ሩብ አመትና የ100 ቀናት እቅድ አፈፃፀማችን ምን ደረጃ ላይ እንዳለ በግልፅ እንገመግማለን ብለው አሁንም ድረስ ጥራትና ውጤታማ ያለው የፕሮጀክት አፈፃፀም ከመተግበር አንፃር፣ ቅንጅታዊ አሰራን በማጎልበትና አቅርቦትን በማሻሻል፣ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አንፃር ጥሩ ጅምር ቢኖርም አሁንም ያልተሻገርነው ችግር አለ ሲሉ ገልፀዋል። አገልግሎት አሰጣጣችን አሁንም ድረስ ከችግር አልተላቀቀም ብለው በምናደርገው የዛሬው ግምገማ በሩብ አመቱ የፈፀምናቸውን አበረታች ውጤቶች ተቀብለን በቀጣይ መፈፀም ያለባቸውን በድክመት የምንለያቸውን ተግባራት ግን በአግባቡ መፍትሔ በምንፈጥርበትና ስኬታማ በምናደርግባቸው ጉዳዮች በግልፅ መገምገም መቻል አለብን ብለው የእለቱን የክቡር እንግዳ ግምገማውን እንዲከፍቱና የስራ መመሪያ እንዲሰጡ ጋብዘዋል ።
ክቡር ዶ.ር አህመዲን መሀመድ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ክላስተር አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በክልላችን ካሉ የኢኮኖሚ ክላስተር ተቋማት በአፈፃፀም የተሻለና ግንባር ቅደም ተቋም ነው፣ ባለፈው አመት እንደ ክልል በበርካታ ችግር ውስጥ ብናልፍም እንደ ተቋም ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል።
እንደሚታወቀው ኢንቨስትመንት እንደሀገር ኢኮኖሚውን ከማሳደግ አንፃር ጉልህ ሚና አለው፣ አሁን ካለንበት የውድድር ግሎባላይዝ አለም አንፃር ይህንን ተቋም ማዘመንና ተወዳዳሪ ማድረግ ለነገ የማይባል ስራ መሆን አለበት። ክልላችንም ኢንቨስትመንት እያደገ የሚሄድበት፣ የእምቅ ሀብት ባለቤት እንደመሆኑ አገልግሎታችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ከማሳለጥና ማዘመን ባሻገር መረጃ አያያዛችንና የአሰራር ስርአታችን ማዘመን የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ
ተግባር ሊሆን ይገባል ብለው፣ ክቡር ዶ.ር አህመዲን በማጠቃለያ ሀሳባቸው ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች በክልላችን ሁሉም መሰረተ ልማት በተሟላላቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮች መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።በቀጣይም በ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም፣ በመስክ ድጋፍ በተገኘው ውጤትና በ100 ቀን እቅድ አፈፃፀምሰፊ ግምገማና ውይይት በማድረግ ግልፅ አቅጣጫ በማስቀመጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።