ክቡር አቶ እንድሪስ አብዱ
የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ
በክልሉ ያሉትን ዘርፈ ብዙ ፀጋዎች ተጠቀመን ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው”
ክቡር አቶ እንድሪስ አብዱ
የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ
ኮምቦልቻ፣ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም (ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ)
የአማራ ክልል “ኢትዮጵያ ታምርት” ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር “ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት” በሚል መሪ መልዕክት በተለያዪ ፕሮግራሞች ዛሬ በኮምቦልቻ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ነው።
በዚህ ወቅት የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ ክልሉ የበርካታ ጸጋዎች ባለቤት መኾኑን ተናግረዋል። ጸጋዎችን ማልማት እና መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። ያለ አምራች እንዱስትሪዎች መስፋፋት ኢኮኖሚን ማሳደግ እንደማይቻልም ገልጸዋል።
ሀገራት ያደጉት ለአምራች ኢንዱስትሪ በሰጡት ከፍተኛ ትኩረት ነው ብለዋል። ባለፉት ዓመታት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች በተሰጠው ትኩረት የአምራች ኢንዱስትሪዎች ተስፋፍተዋል፤ የማምረት አቅማቸው አድጓል፤ በርካታ ባለሃብቶች ወደ ክልሉ መጥተዋል ነው ያሉት።
በክልሉ ያለውን ጸጋ በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችል ዕቅድ ተዘጋጅቶ እየተሠራ መኾኑን ነው ያመላከቱት። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ባለሀብቶች እና መንግሥት የበለጠ እንዲቀራረቡ ያደረገ መኾኑንም አንስተዋል

