የጣና መቀነት የአረንገጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግር ልማት ቀጠና

¨ ይህ ቀጠና  በጣና ሐይቅ ዙሪያ የሚገኙ ከፊል የምዕ/ጎጃም ፣ደ/ጎንደርና የማዕከላዊ ጎንደር አካባቢዎችን እና ባሕር ዳር ከተማን የሚያካልል  ነው ፡፡

¨  ይህ ቀጠና ሰፊ የውኃ ሀብት፣ሜዳማ መልካአምድርራዊ ገፅታ፣ተፈጥሮአዊና ታሪካዊ የቱሪስት መስህቦች የሚገኙበት በመሆኑ ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ፣ለእንሰሳትና የዓሳ ሃብት ልማት ዘርፉ  ፣ለግብርና ውጤት ማቀነባበሪያ( Agro-processing ) ዘርፉ፣ለቱሪዝም ዘርፉ እንዲሁም ለአገልግሎት (ከተማ ልማትና ቴክኖሎጂ ነክ) የተመረጠ ነው፡፡

¨   ስለሆነም በቀጠናው የቅድሚያ-ቅድሚያ የሚሰጣቸው ኢንቨስትመንት ዓይነቶች  ሆቴልና ቱሪዝም፣ሆርቲካልቸር፣የወተት ሀብት ልማት፣የደሮ እርባታና ስጋ ማቀነባበር ፣የዓሳ ሀብት ልማትና የግብርና ውጤቶች ማቀነባበር ፣የከተሞች ልማት እና ፈጠራና ቴክኖሎጂ  ማበልፀግ /ማስፋፋት/ ሥራዎች ናቸው፡፡

¨   የዚህ ቀጠና ዋነኛ ማዕከል ባህርዳር ሲሆን ወረታ ጨምሮ  ሌሎች አዳዲስ ከተሞችን በማልማት በንዑስ የሽግግር ማዕከልነት መጠቀም የሚቻል ይሆናል፡

ለተጨማሪ መረጃ

Scroll to Top