Notice: Function _load_textdomain_just_in_time was called incorrectly. Translation loading for the astra domain was triggered too early. This is usually an indicator for some code in the plugin or theme running too early. Translations should be loaded at the init action or later. Please see Debugging in WordPress for more information. (This message was added in version 6.7.0.) in /data/var/www/vhosts/investinamhara.gov.et/httpdocs/wp-includes/functions.php on line 6260
ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ
Deprecated: Function WP_Dependencies->add_data() was called with an argument that is deprecated since version 6.9.0! IE conditional comments are ignored by all supported browsers. in /data/var/www/vhosts/investinamhara.gov.et/httpdocs/wp-includes/functions.php on line 6260

የቢሮው ኃላፊ መልዕክት

ክልላችን ሰፊ የሚታረስ መሬት÷አመቱን ሙሉ የሚፈሱ ወንዞች÷ገና ያልተነካ ሰፊ የመአድናት ክምችት÷ከፍተኛ የእንስሳት ሀብት÷ በዩኔስኮ የተመዘገቡትን ጨምሮ ለቱሪዝም መስህብነት የሚያገለግሉ ከፍተኛ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ቅርሶች ባለቤት እንዲሁም ሰራ ወዳድና ሰው አክባሪ ህዝብ ያለበት ክልል ነው።

የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮም ክልላችን  ያለውን ሰፊ የሀብት መሰረቶች፣ በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ምቹ ሁኔታዎች በስፋት በማስተዋወቅና ጥቅም ላይ በማዋል ለዜጎች ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠር ፣የውጭ ምንዛሬ ግኝትን፤ የተኪ ምርት መጠንን እና የካፒታል ክምችትን በማሳደግ የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ  ሽግግር ለማፋጠን አልሞ እየሰራ ያለ ተቋም ነው፡፡ በመሆኑም በክልላችን  በጨርቃ ጨርቅና ቆዳ፣ በእንጨትና ብረታብረት፣ በኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓት፣ በአግሮፕሮሰሲንግ፣ በግብርና ልማት፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ በማዕድንና ኢነርጂ፣ በቴክኖሎጂ ልማት÷ በእንሰሳት፤ አበባና ፍራፍሬ  /ሆልቲካልቸር/ ልማት መሰማራት   ለምትፈልጉ  አልሚዎች ክልላችን እጅግ ብዙ እምቅ ሀብቶች ያሉት በመሆኑ ወደ ክልላችን  መጥታችሁ ኢንቨስት እንድታደርጉ እያልኩ ክልላችን  የባለሀብቶችን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ መሰረተ ልማትና የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተሟላላቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በባህር ዳር፣ በኮምቦልቻ፣ በደብረብርሃንና በቡሬ ከተሞች ገንብቶ ለባለሃብቶች በማስተላለፍና ባለሀብቶችን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በተለይ በአግሮ ፕሮሰሲንግ ማለትም በስታርች፣ በግሎኮስ፣በስጋ፣በወተት፣በማር፣በፍራፍሬ እና በሌሎች የግብርና ምርቶች ማቀነባበር ዘርፍ መሰማራት የምትፈልጉ ባለሃብቶች፤ እንዲሁም በጨርቃ ጨርቅ ቆዳና አልባሳት መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች፤  በአጠቃላይ በአምራች ኢንዱስትሪውና በሌሎች ኢንቨስትመንት ዘርፎች   መሰማራት የምትፈልጉ ባለሀብቶች በክልላችን መሰረተ ልማት በተሟላላቸው  ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥም ሆነ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ውጭ በከተሞች እና በከተሞች ዙሪያ ባሉ ለኢንቨስትመንት ተለይተው በተከለሉ ቦታዎች ገብታችሁ ኢንቨስት እንድታደርጉ ስጋብዛችሁ  ታላቅ ደስታ ይሰማኛል፡፡

ክልላችን  ለባለሃቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ፈጣን ፣ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ ከዚህ በፊት በዞኖችና በተወሰኑ ከተሞች ብቻ ተወስኖ የነበረውን አደረጃጀት እስከ ወረዳና ከተሞች ከመዘርጋቱ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከፍቶ  አገልግሎት እየሰጠ መሆኑና የባለሀብቱን እንግልትና ውጣ ወረድ የበለጠ ለመቀነስ  ሲባል አገልግሎቱን ቀልጣፋ÷ግልጽና ፍትሀዊ ሊያደርጉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን አስለምቶ ወደ ስራ እየገባ ያለ መሆኑን ሳሳውቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው ፡፡ አማራ ክልል ሰርተው የሚኮሩበት ፣ነግደው የሚያተርፉበትና በሠላም የሚኖሩበት ክልል ስለሆነ ወደ ክልላችን  መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል፡፡

አቶ እንድሪስ አብዱ
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ
Scroll to Top